Back
Explore every episode of the podcast ዜና መጽሔት
Dive into the complete episode list for ዜና መጽሔት. Each episode is cataloged with detailed descriptions, making it easy to find and explore specific topics. Keep track of all episodes from your favorite podcast and never miss a moment of insightful content.
| Title | Pub. Date | Duration | |
|---|---|---|---|
| የታኅሳስ 11 ቀን የዜና መፅሔት | 20 Dec 2024 | 00:18:20 | |
| የሐሙስ ታኅሣሥ 10 ቀን፣ 2017 ዓ.ም ዜና መጽሄት | 19 Dec 2024 | 00:17:00 | |
| የዐርብ ኅዳር 27 ቀን፣ 2017 ዓ.ም ዜና መጽሄት | 06 Dec 2024 | 00:17:08 | |
| የሐሙስ ኅዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መፅሔት | 05 Dec 2024 | 00:20:55 | |
በዛሬው መጽሔታችን አምስት ርዕሰ ጉዳዮችን በትንታኔ እናስደምጣለን ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጠው መግለጫ ፤ በኦሮሚያ ክልል የታጣቂዎች ለሰላም መመለስ እና የነዋሪዎች አስተያየት ፤ በትግራይ ክልል የቀጠለው እና አወዛጋቢ ሹመቶች እና የነዋሪዎች አስተያየት፤ የአካል ጉዳተኞች ተግዳሮት እና ተስፋ እንዲሁም የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የአንጎላ ጉብኝት እና አንድምታው የተመለከቱ ዘገባዎች በትንታኔ ይደመጣሉ። | |||
| DW Amharic የሕዳር 25 ቀን 2017 የዜና መጽሔት | 04 Dec 2024 | 00:18:38 | |
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት የፓርቲዎች አጀንዳዎችን ለምክክር ኮሚሽን አስረከበ፣ እልባት የሚሻው ያልተቋረጠው የሽርካ ግድያ፤ ደመወዝ ያልተከፈላቸው የአማራ ክልል ሠራተኞች አቤቱታ፣ የነዋሪዎች እሮሮ፣ በደቡብ ኮሪያ የተሞክረው የማርሻል ሕግ(ወታደራዊ አዋጅ) እና መዘዙ | |||
| የኅዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት | 03 Dec 2024 | 00:17:02 | |
የሸማቹ ኑሮ እና የንግድ እንቅስቃሴው እንዴት ሆኖ ይሆን?፤
ትግራይ ክልል ጾታዊ ጥቃት ፈጻሚዎች ተገቢ ርምጃ እንዲወሰድባቸው መጠየቁ፤
አማራ ክልል ጦርነቱ የላሊበላ አስጎብኚዎችንና ነዋሪዎችን ለኑሮ ችግር ዳርጓል
የቦረናዋ ሴት እንድትደበደብ የወሰኑና ድርጊቱን የፈጸመው ተቀጡ | |||
| የሰኞ ኅዳር 23 ቀን 2017 ዓ/ም የዜና መፅሄት | 02 Dec 2024 | 00:18:14 | |
DW Amharic- በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለታጣቂ ቡድኖች ባቀረቡት የሰላም ጥሪ ላይ የተሰባሰበ አስተያየት-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የፓርቲው ኤኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ስኬቶች ሲሉ ስለገለጿቸው ጉዳዮችም ትንታኔ -የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ራሱን የኦሮሞ ነጻ አውጭ ጦር ብሎ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን ጋር የሰላም ስምምነት መፈራረሙን ማስታወቁ-እና ታጣቂ ቡድኑ የክልሉን መንግሥት የሰላም ስምምነት ማስተባበሉ ላይ-የህዝብ አስተያየት - የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያን ጨምሮ ስለ አካባቢያዊ አገራት ጉዳዮች የሰጡት ቃለ ምልልስ በዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን የተካተቱ ጉዳዮች ናቸው ። | |||
| የአርብ ኅዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም.የዜና መጽሔት | 29 Nov 2024 | 00:16:17 | |
የዜና መጽሔት የአንዳራቻ ነዋሪዎች ሥጋት ፤ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሰሞኑ ንግግርና አስተያየት ፤ በምርጫ ቦርድ አስተባባሪነት ሲካሄድ የቆየው የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት መጠናቀቁ፤ እንዲሁም የኦነግ ባለሥልጣን በእስር ላይ ሆነው የጻፉት«ዳያ» ማለትም ራዕይ የተሰኘው «የዓመቱ ምርጥ በኦሮሚኛ የተጻፈው መጽሐፍ»ን የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል | |||
| የኅዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት | 28 Nov 2024 | 00:17:30 | |
የዜና መፅሔት ርዕሶች
ደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ግፊት እየተደረገባቸዉ ነዉ
አማራ ክልል ከ4.7 ሚሊዮን ተማሪዎች አይማሩም
የሕወሃት መሪዎች ዉዝግብ እንደቀጠለ ነዉ
በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት አድርሷል | |||
| የረቡዕ ኅዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት | 27 Nov 2024 | 00:22:51 | |
የወለጋ ሀገር ሽማግለዎች የሰላም ጥሪ፤ አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ መዘግየት ያስከተለው ቅሬታ፤ የሲቪል ማኅበራት እና አመራሮቻቸው እየገጠማቸው ያለው ችግር፤
እንዲሁም የእስራኤልና የሒዝቦላሕ ተኩስ አቁምን የሚመለከቱ ዘገባዎችን አካቷል የዜና መጽሔት። | |||
| የሕዳር 17 ቀን 2017 ዜና መፅሔት | 26 Nov 2024 | 00:17:40 | |
መቋጫ ያላገኘው የስነጾታዊ ጥቃት ማብቂያው መች ይሆን?፤ ትግራይ ክልል ሴቶች ላይ የሚፈፀም ፆታዊ ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ የፀጥታ ችግር የሠቆጣ የምርምር ተቋም ላይ እክል ፈጥሯል እንዲሁም ዶናልድ ትራምፕ ላይ የተመሠረቱ ክሶች ተነሱ። | |||
| የዜና መጽሔት፤ ኅዳር 16 ቀን ቀን 2017 ዓ.ም | 25 Nov 2024 | 00:16:58 | |
| የረቡዕ፤ ታኅሣሥ 9 ቀን፣ 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሄት | 18 Dec 2024 | 00:20:10 | |
የዜና መጽሔት በአማራ ክልል በመንግስት የተጠራ ሰልፍ ዛሬ ስለመካሄዱ እና ስለሰልፉ የፋኖ ምላሽ ላይ ያተኮሩዘገባዎች ቀዳሚ ናቸው ። እሥር ላይ ሆነው በሕመም ውስጥ ስለ ሚገኙት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ይዞታ እንዲሁም የትግራይ ክልል ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ያስከተለው የምሁራን ፍልሰት እና ዶናልድ ትራምፕ ስለ ውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸው የተናገሩትንም አካቷል ። | |||
| ፓስፖርት የማውጣት እንግልት በአማራ ክልል | 22 Nov 2024 | 00:03:57 | |
ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የፓስፖርት መታወቂያ ለማውጣት ወደ ባሕርዳር ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የሚመጡ ተገልጋዮች በተራዘመ ቀጠሮና በከፍተኛ ወጪ በእጅጉ መማረራቸውን ገልጠዋል፡፡ “ፓሰፖርት ለማውታት ለትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎች ብቻ እስከ 12 ሺህ ብር ወጪ እናወጣለን”ብለዋል ተገልጋዮች። | |||
| በኦሮሚያ ክልል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ | 22 Nov 2024 | 00:03:35 | |
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በክልሉ በንጹሃን ላይ የሚፈጸሙ ገግድያዎች እንዲቆሙ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።ሰላማዊ ሰልፉ በዚህ ሳምንት በክልሉ የተፈጸመን አንድ አሰቃቂ ግድያን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መጋራቱን ተከትሎ ነው። | |||
| የዜና መጽሔት፤ ኅዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም | 22 Nov 2024 | 00:17:16 | |
| አዲስ መፅሐፍ በሀረርጌ ኦሮሞ ታሪክ ፣ ባህል እና እሴት ላይ | 22 Nov 2024 | 00:03:22 | |
በሀረርጌ ኦሮሞ ታሪክ ፣ ባህል እና እሴት ላይ በማተኮር የተዘጋጀው መፅሐፍ በሀረር ለምረቃ በቅቷል። በኦሮሚያ ጥናት እና ምርምር ኢንስቲቲዩት በምስራቅ ሀረርጌ አካባቢ በሚኖሩ የሀረርጌ ኦሮሞዎች ታሪክ ላይ የተዘጋጀው መፅሀፍ ማህበረሰቡ ታሪኩን እንዲያውቅ ከማድረግ ባለፈ ትክክለኛውን ታሪክ ለመሰነድ ያስችላል ተብሏል ። | |||
| የሕዳር 12 ቀን 2017 የዜና መጽሔት | 21 Nov 2024 | 00:17:46 | |
በትግራይ 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ማሕበረሰቡ ለመቀላቀል ትጥቃቸው ፈትተው ወደ ስልጠና ማዕከላት የሚገቡበት መረሃ ግብር ዛሬ ተጀመረ።ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ውድቅ እንዲደረግ ተጠየቀ።በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች በንጹሃን ላይ ይፈጸማል ያለው ጥቃት እንዲቆም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ጠየቀ። ሀዋሳ በህጋዊ ማደያዎች ነዳጅ ማግኘት ሲበዛ አዳጋች ነው፡፡ በከተማው የነዳጅ አቅርቦት የለም ፡፡ | |||
| የኅዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት | 20 Nov 2024 | 00:21:46 | |
የዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ከሚያስቃኘን ጉዳዮች መካከል
-የደራ ወረዳው አሰቃቂ ግድያና አላባራ ያለው ውስብስብ ቀውስ
-የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ማዕከል የማስገባት ሥራ ሊጀመር ነው
-የርህራሔ ጠብታ ያለታየበት ጭካኔ
-የአውሮጳ ኅብረት የኅዳር ወር ስብሰባ ትኩረት ይገኙበታል | |||
| የማክሰኞ ኅዳር፤ 10 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዜና መጽሄት | 19 Nov 2024 | 00:19:02 | |
| የዜና መጽሔት፤ ኅዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም | 18 Nov 2024 | 00:18:07 | |
አብዛኛዎቹ የመርካቶ ሱቆች በተቃውሞ ምክንያት ዛሬ ተዘግተው ውለዋል
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አጠቃላይ ጉባኤ ከመጥራቱና አዳዲስ መሪዎችን ከመምረጡ አስቀድሞ ስድስት ፓርቲዎች የጉባኤውን ውጤት እንደማይቀበሉ ተናግረዋል።
በትግራይ በአንድ ሳምንት ውስጥ 17 ሺህ ሰዎች በወባ መያዛቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።
7ኛው ዙር የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ዘመቻ
እነዚህ በዛሬው የዜና መጽሔት ዝግጅታችን ዘገባዎች ትኩረት ናቸው። | |||
| ለ13 አንጋፋ ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ባላሙያዎች እውቅና ተሰጠ | 16 Nov 2024 | 00:02:59 | |
| ለ13 አንጋፋ ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ባላሙያዎች እውቅና ተሰጠ | 16 Nov 2024 | 00:02:59 | |
ታላላቆችን እናክብር በሚል በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ አገራቸውን ያገለገሉ ቀደምት ጋዜጠኞች እና አንጋፋ የመገናኛ ብዙሃን ባላሙያዎችን በዛሬው ዕለት ሽልማት እና ምስጋና ተችሯቸዋል።በዚህ መርሀ- ግብር እንደሚመሰገኑ ከተመረጡ በኃላ ህይወታቸውያለፈውን የሚድያ ሰው ሙልጌታ ወልደሚካኤልን ጨምሮ ለ13 የቀድሞ ጋዜጠኞች ዕውቅ ተሰጥቷል። | |||
| የማክሰኞ ታኅሣሥ 8 ቀን፣ 2017 ዓ.ም ዜና መጽሄት | 17 Dec 2024 | 00:18:25 | |
| በኦሮሚያ፤ተፋላሚዎች ወጣቶችን በግዳጅ ለውትድርና ይመለምላሉ ተባለ | 16 Nov 2024 | 00:03:37 | |
በኦሮሚያ ክልል የሚካሄደውን ግጭት ተከትሎ ተፋላሚዎች ወጣቶችን በግዴታም በውዴታም በስፋት ለውትድርና እየመለመሉ መሆኑን የክልሉ አንዳንድ ነዋሪዎች ገልፀዋል።፡ከተለያዩ አከባቢዎች አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ የሰጡ ነዋሪዎች እንዳሉት እየከፋ መጥቷል ያሉት ይህ መሰሉ ተግባር ለነዋሪው አስጨናቂ ጉዳይ ሆኗል። | |||
| የኅዳር 6 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዜና መጽሔት | 15 Nov 2024 | 00:19:59 | |
የዜና መጽሔት ርዕሰ ጉዳዮች
እርዳታ ካገኘን 2 ዓመት ሆነን” በ2013 ከትግራይ የተፈናቀሉ ወገኖች
የኦሮሚያ ጸጥታ ይዞታ፤ የንጹሃን ጥቃት እና የሰላም ጩኸት
የምስጋና ዝግጅት ለቀድሞዋ የኢትዮጵያ ርዕሠ ብሔር ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ
የጋዛው ጦርነት ተጽእኖ ያደረገበት የፓሪሱ የፈረንሳይና የእስራኤል ብሔራዊ ቡድኖች ግጥሚያ | |||
| የኅዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት | 14 Nov 2024 | 00:17:00 | |
በዛሬው የዜና መጽሔት ከተካተቱት ዘገባዎች መካከል
-የተካረረዉ የኢትዮጵያ እና የሶማልያ የዶፕሎማሲ ዉዝግብ ፤
-በአሙሩ ወረዳ ከሰባት ወራቶች በፊት የታሰሩ ከመቶ በላይ ሰዎች እስከዛሬ ለፍርድ አለመቅረባቸዉና
- በነጩ ቤተ መንግሥት ዉስጥ የተገናኙት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተሰኙት ርዕሶች ስር የተጠናቀሩት ዝግጅቶች ይገኙበታል። | |||
| የሕዳር 4 ቀን 2017 ዜና መፅሔት | 13 Nov 2024 | 00:17:01 | |
በተመድ ስለ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት አያያዝ ምን ተባለ? (ቃለ መጠይቅ)፤ በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የአውሮጳ አምባሳደሮች እንደሚጥሩ መግለጣቸው (ዘገባ)በዶናልድ ትራምፕ መመረጥ የዩክሬን ርዳታ ጉዳይ ያሰጋው የአውሮጳ ኅብረትን በተመለከተ ቃለ መጠይቆች ይኖሩናል | |||
| ማክሰኞ ኅዳር 03 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዜና መጽሄት | 12 Nov 2024 | 00:21:58 | |
| የዜና መጽሔት፤ ህዳር 2 ቀን 2017 ሰኞ | 11 Nov 2024 | 00:17:33 | |
አንጋፋ ባልደረቦቻችን መሸኘት ደጋግሞናል፤ የረዥም ዓመታት ባልደረባችን፤ በኢየሩሳሌም የዶቼ ቬለ ዘጋቢ የነበረው አንጋፋው ጋዜጠኛ እና ደራሲ ዜናነህ መኮንን ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል። በዕለቱ የዜና መጽሔት ከምንዳስሳቸው ጉዳዮች አንዱ ነው፤
ትግራይ ክልል የፖለቲካ ልሂቃን ውዝግብንም የሚያስቃኝ ዘገባ አለን፤ ተመራጩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከወዲሁ ካቢኔያቸውን በማዋቀር እንዲሁም ወደተለያዩ ሃገራት መሪዎች ስልክ በመደወል ተጠምደዋል። የዜና መጽሔት ይህንንም ይዳስሳል። | |||
| የጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ/ም የዜና መፅሔት | 08 Nov 2024 | 00:17:07 | |
አርስተ ዜና፤
--በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን አቸፈር ወረዳ ባለፈው ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 በድሮን በተፈፀመ ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና 9 መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ።
--የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር በፍራንኮ ቫሉታ ሸቀጦችን ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት ከዛሬ ጀምሮ አገደ።
--አቶ ዮሃንስ ቧያሌው 1ኛ ተከሳሽ በሆኑበት መዝገብ የተከሰሱና ጉዳያቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እየታየ ያለው ግለሰቦች ለሕዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ተቀጠሩ።
--በጋዛ ጦርነት ከተገደሉት ውስጥ 70 በመቶ ያህሉ ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸው መለየቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።
ሙሉዉን ዜና ያድምጡ! | |||
| የጥቅምት 28 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዜና መጽሔት | 07 Nov 2024 | 00:22:38 | |
በዕለቱ መጽሄተ ዜና አምስት ጉዳዮችን እናስተነትናለን ።
«ኢሰመኮ 5,568 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ዐሳወቀ» የሚለው ቀዳሚው ነው ።
በሸገር ከተማ ተጀመረ ስለተባለው የመምህራን የት/ቤት ምገባ፤
ትግራይ ክልል መቐለ ለቀድሞ የጦር ጉዳተኞች ሊሰጥ የታቀደው የመኖርያ መሬት እንዲታገድ መጠየቁ
አዲስ ፕሬዚደንት በመረጠችው አሜሪካ የተሸናፊው ፓርቲ ፕሬዚደንት ንግግር ሲያሰሙ፥ የጀርመን ገንዘብ ሚንስትር ተባርረው ተጣማሪዉ መንግስት ፈርሷል ። ቃለ መጠይቆች ይኖሩናል ። | |||
| የረቡዕ፤ ጥቅምት 27 ቀን፣ 2017 ዓ.ም ዜና መጽሄት | 06 Nov 2024 | 00:22:19 | |
| የዜና መጽሔት፤ ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ማክሰኞ | 05 Nov 2024 | 00:22:14 | |
| DW Amharic የዜና መጽሔት፤ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ሰኞ | 16 Dec 2024 | 00:17:47 | |
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በምህጻሩ ኢሰመጉ ዋና ሃላፊ አቶ ዳን ይርጋ የሚደርስባቸው ወከባ በመባባሱ ምክንያት አገር ለቀው መሰደዳቸውን ድርጅቱ ለዶቼቬለ አረጋግጧል። በሌላ በኩል የኢትትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በሦስት ሀገር በቀል የሲቪክ ድርጅቶች ላይ ጥሎት የነበረው እገዳ መነሳቱ ታዉቋል።
ህወሓት በአንዳንድ አካባቢዎች አዳዲስ ሚሊሽያዎችን እየመለመለ ነው፣ በሕገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮ ላይም ተሰማርቷል ሲሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከሰሱ።
ከ 3 ሺህ በላይ «የአዋሽ ኮምቦልቻ ሃራ የባቡር መንገድ ፕሮጀክት» ሠራተኞች ያለፉት 9 ወራት ደሞዛችን አልተከፈለንም ሲሉ ለዶቼቬለ ተናገሩ። | |||
| የጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም የዜና መጽሔት | 04 Nov 2024 | 00:19:22 | |
ቁጣን ያስከተለው የደራ ኢማም ግድያ፤
የዉይይት ርእስ ሆኖ የቀጠለው የኢትዮጵያ ሰላም ጉዳይ፤
ደሞወዝ ያልተከፈላቸዉ መምህራን በፌደራሉ መንግስት እና በክልሉ አስተዳደር ላይ ክስ መመስረታቸዉ ፤እንዲሁም
ነገ የሚካሄደዉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት የሚወስኑት ሰባት የአሜሪካ ግዛቶች | |||
| የጥቅምት 22 ቀን 2017 ዜና መፅሔት | 01 Nov 2024 | 00:21:11 | |
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥት እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ግጭት ለማቆም ሥምምነት የተፈራረሙት ጥቅምት 23 ቀን 2015 ነበር። የትግራይ እና የአማራ ክልሎች ነዋሪዎች ስለ ሥምምነቱ አፈጻጸም ምን ይላሉ? | |||
| የጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ,ም. የዜና መጽሔት | 31 Oct 2024 | 00:16:06 | |
DW Amharic-የጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ/ም የዜና መጽሔት
በዛሬው የዜና መፅሄት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤት ተገኝተው የሰጡት ማብራሪያ፤
ከሰሞኑ ነቀምቴ ውስጥ የተደፈረችው አዳጊ «አሁን ከሕግ ፍትህ እሻለሁ” ትላለች፤
በአማራ ክልል ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሰብል ላይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑ
ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ ሳይንስ ላይ የሚያተኩሩ የዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት መመስረቱን አካቷል። | |||
| የረቡዕ፤ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም የዜና መጽሔት | 30 Oct 2024 | 00:19:00 | |
አንድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት ሶማሊያን በ72 ሰዓታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ፤
እስር፤ ግድያና እገታ በጉራጌ ዞን፤
የሲቪል ማኅበረሰብ ምህዳር የመዳከም ሥጋት
ስለ ካማላ ሐሪስ የምርጫ ቅስቀሳ መዝጊያ ጎናጭ ንግግር ቃለ-መጠይቅ | |||
| የማክሰኞ፤ ጥቅምት 19 ቀን፣ 2017 ዓ.ም ዜና መጽሄት | 29 Oct 2024 | 00:22:31 | |
የዜና መፅሔት ጥንቅራችን አምስት ጉዳዮችን ያስተነትናል። ዜና መፅሔቱ አዲስ አበባ ላይ የአዲሱ የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሹመት፣ መቀሌ ደግሞ የከንቲባ መሻር ያስነሳዉን ጥያቄ፣ ቅሬታና ዉዝግብ የሚቃኙ ዘገቦችን ያስቀድማል።ምሥራቅ ወለጋ ነዋሪዎች ትጥቅ እንዲፈቱ መወሰኑ ያሳደረዉ ሥጋት፣ በአማራ ክልል የሚሞቱ እናቶች ብዛት መጨመርና በደቡብ ክልል የወባ በሽታ መስፋፋቱን የሚያወሱ ዘገቦችም አሉት። | |||
| የዜና መጽሔት፤ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ሰኞ | 28 Oct 2024 | 00:13:53 | |
| የጥቅምት 15 ቀን 2017 ዜና መፅሔት | 25 Oct 2024 | 00:18:07 | |
በዎላይታ ዞን የመምህራን እሥር እየተካሄደ ነው መባሉ፤ ኢትዮጵያ አዲስ ሕገ መንግሥት ያስፈልጋታል ያሉ ወገኖች በዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት ያካሄዱት ውይይት፤ በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰበት አል ነጃሺ መስጊድ ጥገና መጀመሩ፤ እንዲሁም የመካከለኛዉ ምሥራቅ ጦርነት፣ የአሜሪካ ዲፕሎማሲና የየገንዘብ መዋጮን የሚያስቃኙ ዘገባዎችን አካቷል የዜና መጽሔት | |||
| የጥቅምት 14 ቀን 2014 ዓ/ም የዜና መጽሔት | 24 Oct 2024 | 00:25:14 | |
| የዜና መጽሔት ማስተዋወቂያ | 24 Oct 2024 | 00:01:00 | |
በዐበይት የኢትዮጵያ፣ የአፍሪቃ፣ የአውሮጳ እና የዓለም ጉዳዮች ላይ ዘገባዎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና ጥልቅ ትንታኔዎች ይቀርባሉ። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የዶይቼ ቬለ ዘጋቢዎች የሚያጠናቅሩት ዜና መጽሄት ከሰኞ እስከ አርብ ከዓለም ዜና ቀጥሎ ይቀርባል። የዶይቼ ቬለን ሥርጭት በራዲዮ እና በሳተላይትም በፌስቡክ በቀጥታ ማድመጥ ይቻላል። በዩቲዩብ፣ በአፕል ፖድካስት፣ በስፖቲፋይ እና በየትኛውም የፖድካስት ምርጫዎን በምታገኙባቸው መንገዶች የዶይቼ ቬለን ዜና መጽሔቶች ማድመጥ ትችላላችሁ። | |||
| የጥቅምት 13 ቀን 2017 የዜና መፅሄት | 23 Oct 2024 | 00:20:09 | |
በዜና መፅሔት ጥንቅሩ
አስገድዶ መሰወር፣ እገታ እና እየደረሰ ያለው ቀውስ፣የትግራይ ነጻነት ፓርቲና የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ውዝግብ፣ከእርዳታ አውጡን» የአማራ ክልል ተፈናቃዮች፣የመሬት መንቀጥቀጥና የአዲስ አበባ ሕንጻዎች እና ኢትዮጵያን በሕክምና የዕውቀት ሽግግር ለማገዝ የሚጥረው «ፒፕል ቱ ፒፕል ያልናቸዉን ጉዳዮች ያስተነትናል። | |||
| የታኅሳስ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. የዜና መጽሔት | 13 Dec 2024 | 00:16:30 | |
የዜና መጽሔት ዝግጅታችን፤
የአንካራው ስምምነት የኢትዮ-ሶማሊላንድ ስምምነትን ይሽራልን?
የስልጣን ርክክብ የተደረገባት ሶማሌ ላንድ የኢትዮጵያና ሶማልያን ስምምነት ብሎም ስለመግባብያ ስምምነቱ ምን ብላ ይሆን ቃለ ምልልስ ይዘናል። እንዲሁም
- በህዝብ ተሳትፎ ይሰራል የተባለው የወሎ ሆስፒታል ግንባታ የሀብት ብክነት አጋጠመው መባሉን ያስቃኘናል። | |||
| የጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም የዜና መጽሔት | 23 Oct 2024 | 00:19:07 | |
መርካቶ-አዲስ አበባ ዉስጥ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ ብዙ ንብረት አወደመ
በኮሬ ዞን በተጋጋሚ ሰዎች መገደላቸዉና የነዋሪዎች ሥጋት
ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ተሸለመ
የአፍሪካ የፀጥታው ምክር ቤት ውክልና ጉዳይ | |||
| የጥቅምት 11 ቀን 2017 መፅሔተ ዜና | 21 Oct 2024 | 00:17:35 | |
| የጥቅምት 8 ቀን 2017 የዜና መፅሔት | 18 Oct 2024 | 00:16:25 | |
| የሐሙስ፤ ጥቅምት 7 ቀን፣ 2017 ዓ.ም ዜና መጽሄት | 17 Oct 2024 | 00:25:39 | |
© My Podcast Data · Independent project · Data from Apple & Spotify