Back
Explore every episode of the podcast የዓለም ዜና
Dive into the complete episode list for የዓለም ዜና. Each episode is cataloged with detailed descriptions, making it easy to find and explore specific topics. Keep track of all episodes from your favorite podcast and never miss a moment of insightful content.
| Title | Pub. Date | Duration | |
|---|---|---|---|
| የዓለም ዜና፤ ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም የዓለም ማክሰኞ | 13 oct. 2026 | 00:11:56 | |
በአማራ ክልል ዉስጥ በደቡብ ወሎ ና በሰሜን ሸዋ አካባቢዎች ዉግያ እየተካሄደ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ።-ሰሜን ኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣዉ ጦርነት የተለያዩ ፍላጎቶች ያላቸው አገራትን በመጋበዝ በቀጣናው አላስፈላጊ ሰብዓዊና የንብረት ውድመት ከማስከተሉ በፊት ዓለማቀፉ ማህበረሰብ፤ ግፊት እንዲያደርግ ኦነግ አሳሰበ፡፡ | |||
| የጥቅምት 2 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና | 12 oct. 2026 | 00:10:08 | |
የኢትዮጵያ ፌደራል ኃይሎችና ተባባሪዎቻቸው አደዋ ከተማ መግባታቸውን ነዋሪዎች አመለከቱ።
ከጅቡቲ ወደ የመን ለመጓዝ አልማ አደጋ ባጋጠማት ጀልባ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 139 መድረሱን IOM አመለከተ።
በሱዳን ግብፅ ድንበር በአየር ጥቃት 72 ሰዎች መገደላቸው ተገነገረ።
የተመ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን የበጀት እጥረት እንደገጠመው አስታወቀ። | |||
| የጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም የዓለም ዜና | 11 oct. 2026 | 00:09:30 | |
የዛሬው የዓለም ዜና በትግራይ ለምርጫ አስቻይ ሁኔታ እስኪፈጠር ክልሉ በቀጥታ በፌደራል መንግስቱ ስር ሊተዳደር ይችላል መባሉን፣በጂቡቲ በጀልባ አደጋ ከ100 በላይ ስደተኞች መሞታቸውን፣ሁቲዎች መንገደኞች የሪያድ አየር ማረፊያዎችን እንዳይጠቀሙ ማስጠንቀቃቸውንና ሌሎችን አካቷል። | |||
| የመስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና | 10 oct. 2026 | 00:11:53 | |
ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ ራስን የመከላከል እርምጃ እየወሰደች መሆኗን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ዐስታወቀች ። ኤርትራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት በኢትዮጵያ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር የሚችል እርምጃ እንዲወስድ ጠየቀች። | |||
| የዓለም ዜና፤ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም አርብ | 09 oct. 2026 | 00:11:58 | |
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ካቋረጡ ከጥቂት ቀናት በኋላ አንዱ አንዱን ፣ "የጥቃት ጦርነት" ጀምሮብኛል ሲሉ መወነጃጀል ጀመሩ። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፤ በመቀሌ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች፣ ሰላምና ስርዓትን ወደነበረበት ለመመለስ እንዲተባበሩ ለነዋሪዎች ጥሪ ማቅረቡ ተሰማ። | |||
| የመስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና | 08 oct. 2026 | 00:11:46 | |
የመስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና | |||
| የመስከረም 27 ቀን 2019 የዓለም ዜና | 07 oct. 2026 | 00:11:59 | |
-የኢትዮጵያ መንግሥት ጦር ከአዲግራት ወደ መቀሌ ይጓዝ የነበረ የኤርትራ ጦር ቅፍለትን በሰዉ አልባ አዉሮፕላን መምታቱ ተነገረ።-የየመን አንሳር አላሕ ቡድን የአደንና የሪያድ አዉሮፕላን ማረፊያዎችን መደብደቡ ተዘገበ።---እስራኤል በሐማስ የተጠቃችበት ሶስተኛ ዓመት ዛሬ በሐዘን፣በፀሎት፣በስብሰባና በአደባባይ ሰልፍ ተዘክሮ ዋለ። | |||
| የመስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና | 06 oct. 2026 | 00:10:01 | |
የተመድ ሱዳን ውስጥ ሲቪሎች ላይ የሚፈጸም ጥቃትን አወገዘ።
የመን ውስጥ በሁቲ አማጽያንና በመንግሥት መካከል በሚደረገው ውጊያ ከ184 ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ።
ሳውድ አረቢያ ሁለት የአውሮፕላን ማረፊያዎቿ መመታታቸውን አስታወቀች።
በጀርመን ዛክሰን አንሀልት ፌደራል ግዛት የአማራጭ ለጀርመን ለም/ቤት አፈ ጉባኤነት ተመረጠ። | |||
| የመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና | 05 oct. 2026 | 00:10:04 | |
የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት 7ኛ መደበኛ ስብሰባ 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመንግስት ምስረታ ጉባኤውን በማካሄድ ዶክተር አብይ አሕመድን በጠቅላይ ሚኒስት አድርጎ ሰይሟል።ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝና በቀይ ባሕር ያላትን ታሪካዊና መልከዐምድራዊ እውነታዎች በማንኛውም ኃይል ሊቀየር አይችልም ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። | |||
| የመስከረም 24 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና | 04 oct. 2026 | 00:07:54 | |
የመቐለ ከተማን ለቆ የወጣው ህወሓት መራሹ «የትግራይ ክልል መንግስት» በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች እንደሚቀጥሉ አስታወቀ። የህወሓት ባለስልጣናት የመቐለ ከተማን ለቀው ሲወጡ ቆስለው በህክምና ላይ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎችን ይዘው መውጣታቸውን የሆስፒታል ምንጮች ለዶቼ ቬለ ተናገሩ። | |||
| የመስከረም 23፣ 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና | 03 oct. 2026 | 00:09:55 | |
• የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እና አጋር ኃይሎች የትግራይ ክልል መዲና መቀሌን ተቆጣጠሩ።
• የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ዛሬ ጠዋት ወደ ግብጽ ካይሮ ተጓዙ ።
• የ2019 የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ዛሬ በድምቀት ተከበረ። | |||
| የመስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም የዓለም ዜና | 02 oct. 2026 | 00:10:57 | |
የትግራይ ሰላም ሀይል ከመቀለ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለች ከተማን ተቆጣጠርኩ ማለቱን፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላማዊ ሰዎች ላይ ሞት፣ መፈናቀልና ሰብአዊ ቀውስማድረሱን፣ግብፅ የኢትዮጵያን ዲፕሎማት ከሀገሯ ማስወጣቷን፣የአፍሪቃ ሕብረት በኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ግብፅ መካከል ውጥረት እንዲረግብ ጥሪ ማቅረቡን እና ሌሎችን አካቷል። | |||
| የመስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና | 01 oct. 2026 | 00:11:26 | |
ትናንት ምሽት በአዲስ አበባ ፍንዳታ መሰማቱን ሮይተርስን ጨምሮ የተለያዩ የዜና አውታሮች ዘገቡ።
ኢትዮጵያ አስመራ ያለውን ኤምባሲ ለመዝጋት ወሰነች።
በሰሜን ኢትዮጵያ የፀጥታ ስጋቱ የሰብአዊ አቅርቦትን ማስታጎሉን የተmm,ድ ገለጸ። እስራኤል በፍላይ ዱባይ አውሮፕላን ውስጥ የተከሰተውን ጥቃት ከመሠረቱ እንደምታጣራ ዛተች። | |||
| የመስከረም 20 ቀን 2019 የዓለም ዜና | 30 sept. 2026 | 00:11:42 | |
-የኢትዮጵያ ተፋላሚ ኃይላት የድርድርን መንገድ እንዲመርጡ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ተማፀኑ።ዉጊያ እንደቀጠለ ነዉ።-- አዲስ አበባና አካባቢዋ ሰዉ አልባ አዉሮፕላን እንዳይበር ታገደ።-ኢትዮጵያን ጨምሮ ለምሥራቅ አፍሪቃ ሐገራት ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣል የተባለ ግዙፍ የነዳጅ ማጣሪያ ግንባታ ላሙ-ኬንያ ዉስጥ ተጀመረ። | |||
| የዕለተ ማክሰኞ መስከረም 19 ቀን፣ 2019 ዓ.ም የዓለም ዜና | 29 sept. 2026 | 00:08:36 | |
ዋሽንግተን፥ ማርኮ ሩቢዮ የኢትዮጵያን ውጥረት ለማርገብ አፋጣኝ ርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ቀረበ፣ አ.አ፥ በሰሜኑ ጦርነት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው ተገለጠ፣ ወሎ፥ በተቀሰቀሰው ጦርነት የተፈናቃዮችን መከራ ማባሱ ተገለጠ፣ ካይሮ፥ የአፍሪቃ አገራት ለንድግ ግብጽ ውስጥ ይሰበሰባሉ፣ ፑንትላንድ፥ አንዲት ነዳጅ ጫኝ መርከብ ከባሕር ላይ ዘራፊዎች ነጻ ወጣች | |||
| የዓለም ዜና | 28 sept. 2026 | 00:11:58 | |
በዛሬው የዓለም ዜና በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በተለያዩ ከተሞች የበርክታ ሰላማዊ ሰዎች ህይወት ማለፉን ፤የትግራይ የቴሌቪዥን ጣቢያ በድሮን ተመታ ባሉን፣ ቀይመስቀል 161 ሰዎችን ግጭት ካለባቸው አካባቢዎች ዛሬ ማስወጣቱን፣በሽብርተኝነት ተከሰው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የነበሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች አስጊ ወደተባሉ እስር ቤቶች ተዛወሩ መባሉን አካቷል። | |||
| የመስረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና | 27 sept. 2026 | 00:08:19 | |
በሰሜን ኢትዮጵያ በቆቦና አላማጣ አካባቢዎች ከባድ ውግያ ሲካሄዱ እንደዋሉ መረጃዎች አመላከቱ። አላማጣ፣ ጥሙጓና ሰሌን ውሃ በፌደራል መንግስት ቁጥጥር ስር መሆናቸውን ታውቋል። በመቐለ ከተማ በሚገኘው የትግራይ ቴሌቪዥን የድሮን ጥቃት እንደተፈጸመበት የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። | |||
| DW Amharic የመስከረም 16 ቀን 2019 የዓለም ዜና | 26 sept. 2026 | 00:10:56 | |
ሩሲያና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ግጭት ያሳስበናል አሉ። መከላከያ ሠራዊት በትግራይ አምስት ትምህርት ቤቶች እና በአማራ ክልል ቆቦ ከተማ ላይ በፈጸማቸው ድብደባዎች ሰዎች መገደላቸውን የተመ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል። በመቐለ መከላከያ ሠራዊት የፈጸመው ጥቃት እንደ “የጦር ወንጀል ሊመረመር እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ። | |||
| የመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም. የዶቼቬለ የዓለም ዜና | 25 sept. 2026 | 00:11:46 | |
አርዕስተ ዜና
-የኢትዮጵያ ጦርና የትግራይ ኃይሎች ዛሬ በተለያዩ ግንባሮች ከባድ ውጊያ መካሄዳቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገበ
-በትግራይ ክልልና በአማራ ክልል አንዳንድ ከተሞች የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት ዛሬ አርብ መታጎሉን ተጠቃሚዎች አስታወቁ ።
-በሰሜን ኢትዮጵያ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች ፍርሀት ውስጥ እንደሚገኙ ተናገሩ። | |||
| የመስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና | 24 sept. 2026 | 00:10:41 | |
የትግራይ ኃይሎች ከፌድራል መንግሥት ጋር “ሙሉ ጦርነት” መግጠማቸውን ገለፁ። የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ጦርነት “በአፋጣኝ ማርገብ” እንደሚያስፈልግ አሳሰበ። ኢትዮጵያን ከጅቡቲ የሚያገናኝ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ልትዘጋ ነው። ዩናይትድ ስቴትስ ፑቲንን ለቡድን 20 ጉባኤ ጋበዘቻቸው | |||
| የመስከረም 13 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና | 23 sept. 2026 | 00:10:18 | |
የኢትዮጵያ የፈደራል መንግሥትና ትግራይን የሚገዛዉ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ኃይላት አዲስ ዉጊያ ገጥመዋል።የደቡብ ሱዳን ፕረዝደንት ሳልቫኺር የሐገሪቱን የሽግግር መንግስት አፈረሱ። ኢራን በአሜሪካና እስራኤል ጥቃቶች የወደመውን የነዳጅ ማምረቻ መሰረተ ልማቶች መልሶ ግንባታ 50 በመቶ ማጠናቀቋን አስታወቀች። | |||
| News AMH_am Dienstag den 22.09.2026 - MP3-Stereo | 22 sept. 2026 | 00:11:36 | |
የኢትዮጵያ የፀጥታ ሁኔታ አሳስቦኛል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። በሃገሪቱ ውጥረቶችን ለመቀነስ እና የፕሪቶሪያ ስምምነትን ተግባራዊ ለማድረግ በአፍሪቃ ኅብረት የሚመራውን ጥረት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መደገፉን እንደሚቀጥል ተናግረዋል። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ኒዮርክ ላይ በይፋ ጀመረ። | |||
| የመስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና | 21 sept. 2026 | 00:11:57 | |
አርዕስተ ዜና
-የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የትግራይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከስርጭት መታገዱን አስታወቀ።
-የየመን ሁቲዎች ስልታዊ የተባሉ የየመን ከፍተኛ ስፍራዎችን ለመቆጣጠር በመገስገስ ላይ ናቸው
- የጀርመን ክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት ፓርቲ ሜክለንቡርግ ፎር ፖመርን ግዛት ፓርላማ መግባት ሳይችል ቀረ | |||
| የመስከረም 10 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና | 20 sept. 2026 | 00:07:59 | |
ሰባት ታጣቂ ቡድኖች የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና የተባለ ጥምረት መመሥረታቸውን አወጁ ። አሜሪካ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት ከፈጸመች በመካከለኛ ምስራቅ ውስጥ የሚገኙ የጦር ሰፈሮቿንና ጥቅሞቿ ላይ ጽኑ ሕመን የሚያስከትል ጥቃት እንደምትፈጽም ኢራን አስጠነቀቀች። | |||
| የመስከረም 9 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና | 19 sept. 2026 | 00:11:20 | |
• በደቡባዊ ትግራይ ማይጨው ከተማ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን የክልሉን የመገናኛ ብዙኃን ጠቀሶ የትግራይ ቴሌቭዥን በፌስ ቡክ ገጹ ዘገበ። • በጋምቤላ ክልል ታጣቂዎች በሕዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ላይ ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 10 ሰዎች ተገደሉ ። ሌሎች በርካቶች ቆሰሉ። • ሳዑዲ አረቢያ መዲና ሪያድ ውስጥ የፍንዳታ ድምፅ መሰማቱ ተዘገበ ። | |||
| የመስከረም 8፣ 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና | 18 sept. 2026 | 00:12:27 | |
• የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት 300 ያህል የትግራይ ታጣቂ ኃይሎች አባላት እጃቸውን መስጠታቸውን አስታወቀ። • የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሠ) የኢትዮጵያ መንግስትን በጋራ “ለመዉጋት” የተመሠረዉ “ፅምዶ” ተባለ ህብረት ውስጥ ተሳትፎ እንደሌለውና የትብብሩ አባል አለመሆኑን አስታወቀ፡፡ | |||
| የዓለም ዜና፤ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም | 17 sept. 2026 | 00:10:39 | |
አርስተ ዜና፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንሶ ዞን ከጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አደረሱት በተባለው ጥቃት ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ገለጹ።-የስምረት ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ፤ ትምህርት ሚኒስቴር ን እርምጃ አወደሰ። ሜሪካ ለደቡብ አፍሪቃውያን አዲስ የቪዛ ገደብ ፖሊሲ ማዉጣትዋን አስታወቀች። | |||
| የመስከረም 6 ቀን 2019 የዓለም ዜና | 16 sept. 2026 | 00:10:51 | |
-ሊቢያ ዉስጥ በየእስር ቤቱ የሚገኙ የኤርትራ ሥደተኞች ከፍተኛ ሥቃይ እንደሚደርስባቸዉ አስታወቁ።ሥደተኞቹ እንደሚሉት የየእስር ቤቱ ተቆጣጣሪዎችና ጠባቂዎች።ይደበድቧቸዋል።ሴቶቹን ይደፍሯቸዋል።---የየመን አንሳር አላሕ ተዋጊዎች የሙስሊሞቹን ቅድስት ከተማ መካን ለማጥቃት ሞከራዋል የሚለዉን የሪያድ ገዢዎችን ክስ አስተባበሉ። | |||
| የመስከረም 5 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና | 15 sept. 2026 | 00:10:45 | |
• በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትናንት ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የአስራ ሦስት ሰዎች ህይወት አለፈ ፡፡
• የትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚመደቡ ተማሪዎችን ማመልከቻዎች መቀበል መጀመሩን አስታወቀ። | |||
| የመስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና | 14 sept. 2026 | 00:11:55 | |
የመስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንሶ ዞን ታጣቂዎቸ አደረሱት በተባለው ጥቃት 5 ሰዎች ተገደሉ፤ 4 ደግሞ ቆሰሉ።
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል እሁድ ለሊት ለሰኞ አጥቢያ በሱዳኑ የብሉ ናይል ግዛት በአል-ዳማዚን ከተማ የድሮን ጥቃት ፈፀመ ።
የሁቲ አማጽያን ዛሬ የሀኒሽ ደሴቶችን ተቆጣጠሩ ። | |||
| የመስከረም 03 ቀን 2019 የዓለም ዜና | 13 sept. 2026 | 00:08:31 | |
በየመን በሑቲዎችና የመንግሥት ኃይሎች ውጊያ 86,000 ሰዎች ሲፈናቀሉ ከ2,000 በላይ ጅቡቲ ገቡ። “በዓለም ዙሪያ የግጭቶችና ውጥረቶች ቁጥር እየጨመረ” በመሔዱ በሕዝቦች ሕይወት ላይ ሰፊ ተጽዕኖ ማሳደሩን የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አስጠነቀቁ። ሩሲያ ከዋርሶ ወደ ኪየቭ በተዘረጋ ባቡር ላይ ጥቃት መፈጸሟን ፖላንድ አስታወቀች። | |||
| የመስከረም 2 ቀን 2019 ዓ/ም የዓለም ዜና | 12 sept. 2026 | 00:11:48 | |
ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናን እያተራመሰች ነው ስትል ኤርትራ ከሰሰች። ለብሪክስ ጉባኤ ሕንድ ኒውደልሂ ከተማ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከስብሰባው ጎን ለጎን የኢራን ፕረዚደንትን ጨምሮ ከተለያዩ ሐገራት መሪዎች መወያየታቸውን ገለፁ።ኢራቅ ከኢራን ጋር የሚያዋሱኗት ሦስት ድንበሮች ዛሬ መዝጋቷን አስታወቀች። | |||
| የመስከረም አንድ ቀን 2019 ዓ.ም. የዓለም ዜና | 11 sept. 2026 | 00:10:50 | |
በአሜሪካን በኒውዮርክ፣ በፔንታገንና በፔንሲልቬንያ የተፈጸመው የሽብር ጥቃት 25 ተኛ ዓመት ዛሬ በአሜሪካን በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየታሰበ ነው።
ነገ ህንድ ውስጥ በሚጀመረው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የአባል ሀገራት መሪዎች ኒውዴልሂ እየገቡ ነው።
የሁቲ አማጻያን ዛሬ ስልታዊ የሚባለውን ፔሪም ደሴትንና የዱባብ ከተማንም ይዘዋል | |||
| የጳጉሜ 5 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና | 10 sept. 2026 | 00:10:35 | |
አ.አ፥ ከ600 እስረኞች በላይ መለቀቃቸውን ኢሰመኮ ዐሳወቀ፤ ጊምቢ፥ አልጄሪያ ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን አቋረጠች፤ ሣንዓ፥ የሑቲ ዓማጺያን በቀይ ባሕር ቁልፍ የወደብ ከተማን ተቆጣጠሩ፤ ዋሽንግቶን፥ ዶናልድ ትራምፕ ፓርቲያቸው በአማካይ ዘመን ምርጫ ካሸነፈ ለእያንዳንዱ አዋቂ 5ሺህ ዶላር ሊሰጡ ቃል ገቡ | |||
| የጳጉሜ 4 ቀን 2018 የዓለም ዜና | 09 sept. 2026 | 00:12:19 | |
-- የአሸባሪነት ክስ የተመሰረተባቸዉ የኢሕአፓ መሪዎችና ጠበቃ በዋስ እንዲፈቱ የተላለፈላቸዉ ዉሳኔ ታገደ።-ብሪታንያ ምሥራቃዊ እየሩሳሌም ዉስጥ የሚገኝ የቆንስላ ጽሕፈት ቤቷን እንድትዘጋ እስራኤል ማሳሰቧን ብሪታንያ የሚጠበቅ፣ግን አሳዛኝና ግንኙነትን የሚያበላሽ በማለት ነቀፈችዉ።-የዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ዉጊያ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ። | |||
| የዓለም ዜና፤ ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ማክሰኞ | 08 sept. 2026 | 00:12:28 | |
አርስተ ዜና፤ በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል በሚገኝ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ በተፈጸመ ጥቃት በርካቶች ሞቱ። -በትግራይ ክልል የሚገኙ አማፅያን የኢትዮጵያ መንግስት በክልሉ ሌላ የድሮን ጥቃት ፈፅሟል አሉ።-በሌላ በኩል በትግራይ እየተፈፀመ ያለዉ የወጣቶችና የታዳጊ ልጆች አፈሳ ይቁም ሲሉ በትግራይ ክልል አዲግራት ከተማ እናቶች ለተቃዉሞ ወጡ። | |||
| የጳጉሜ 02 ቀን 2018 የዓለም ዜና | 07 sept. 2026 | 00:11:03 | |
የትግራይ ክልል ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ “ገለልተኛ አይደሉም” በማለት ወነጀለ። በኢትዮጵያ ውጊያ የገጠሙ ኃይሎች በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን እንዲያቆሙ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ጥሪ አቀረቡ። መራኄ መንግሥት ፍሬድሪሽ ሜርስ ቀኝ አክራሪው አማራጭ ለጀርመን ያስመዘገው የምርጫ ድል ፓርቲያቸውን ከመሠረቱ እንደነቀነቀ ተናገሩ | |||
| የጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና | 06 sept. 2026 | 00:08:03 | |
በየመን መንግስት ኃይሎችና «በኢራን ይደገፋሉ» የሚባሉት የሑቲ ደፈጣ ተዋጊዎች መካከል ትላንት አገርሽቶ እስከ ዛሬ በተካሄደ ውግያ ከሁለቱም ወገን ከ140 በላይ ወታደሮች መገደላቸውን ተሰማ። በምሥራቅ ጀርመን በምትገኘው የዛክሰን አንሃልት ግዛት የአካባቢ ምርጫ እየተካሄደ ነው። | |||
| የነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና | 05 sept. 2026 | 00:11:13 | |
• በደቡብ ሱዳን ሰሜናዊ ምስራቅ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 20 ሰዎች ተገደሉ ። አስራ ስድስቱ የመንግስት ወታደሮች እና ፖሊሶች ናቸው ። • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን አህጉር ትክክለኛ ስፋት የሚያሳይ አዲስ የዓለም ካርታ ጥቅም ላይ እንዲውል የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ አፀደቀ። | |||
| የነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና | 04 sept. 2026 | 00:11:48 | |
በኢትዮጵያ በሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የኮምፒውተር ቤተ-ሙከራ ለማቋቋም ወደ 38,000 ኮምፒውተሮች እንደሚያስፈልግ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ ተናገሩ። | |||
| የነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና | 03 sept. 2026 | 00:10:57 | |
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተነሳ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሾመው የሱዳን ጉዳይ የምርመራ ቡድን፤ የውጭ ሐገራት ታጣቂዎች በሐገሪቱ ያለውን ግጭት እያባባሱት ነው ሲል ከሰሰ። የእስራኤል ጦር አባላት በምዕራባዊ ዮርዳኖስ የባሕር ዳርቻ 2 ፍልስጤማውያን ወጣቶችን ተኩሰው መግደላቸውን | |||
| የነሐሴ 27 ቀን 2018 የዓለም ዜና | 02 sept. 2026 | 00:12:00 | |
-የጀርመንና የሩሲያ ተዘዋዋሪ ግጭት ወደ ቀጥታ ዉዝግብ፣ የጥቃት ሙከራ፣ ቅጣትና የአፀፋ ቅጣት ዛቻ ንሯል።---የቻይና መሪ ሺ ጂፒንግ የዉጪ መንግሥታት በመካከለኛዉ ምሥራቅ የዉስጥ ጉዳይ ጠልቃ እንዲገቡ የአካባቢዉ መንግሥታት መፍቀድ የለባቸዉም አሉ።-ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን አንዳቸዉ የሌላቸዉን ተቋማትና ጥቅሞች መደብደባቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ። | |||
| የነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና | 01 sept. 2026 | 00:11:37 | |
አርዕስተ ዜና
የኬንያ የአቪዬሽን ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማቸውን ማቋረጣቸው ተገለፀ ።
የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሀካይንዴ ሂቺሌማ ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን ዛሬ ቃለ መሀላ ፈጸሙ ።
የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽክያን ሩሲያ በመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ላይ ለያዘችው አቋም ፑቲንን አመሰገኑ። ፑቲንም ፔሽኬቭያንን ለተጋድሎአቸው አወደሱ | |||
| DW Amharic የነሐሴ 25 ቀን 2018 የዓለም ዜና | 31 août 2026 | 00:11:22 | |
በአንድ ሣምንት 2,463 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግሥት ከ6,000 በላይ ሰዎች በኢቦላ መያዛቸውን አረጋገጠ። በሱዳን የታቀደው ብሔራዊ ውይይት “የመጨረሻ ግብ በሕጋዊ ሲቪል ተቋማት የምትመራ፣ አንድ ወጥ ብሔራዊ የጸጥታ መዋቅር” ያላት “የተባበረች፣ ሉዓላዊ እና ሰላማዊ” አገር መፍጠር ሊሆን እንደሚገባ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን መከረ። ሕንድ ከፓኪስታን ጋር የተፈራረመችውን የውኃ መጋራት ሥምምነት እንድታከብር በፍርድ ቤት የተላለፈባትን ውሳኔ ውድቅ አደረገች። የአሜሪካና ኢራን ጦርነት ዳግም ሲያገረሽ በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ጨመረ። | |||
| የነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና | 30 août 2026 | 00:08:33 | |
የዛምቢያ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ በሐገር ክህደት ወንጀል እንደተከሰሱ የሐገሪቱ አቃቤ ሕግ አስታወቀ። በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ በወታደሮች ተቀስቅሶ የነበረው ዓመጽ በኒጀር መንግስት ታማኝ ወታደሮችና በሐገሪቱ ያሉ የሩስያ የአፍሪካ ጓድ ጦር አባላት ድጋፍ መክሸፉን ተከትሎ ከተማዋ በዛሬው ዕለት አንጻራዊ ሰላም ማግኘቷን ተነገረ። እስራኤል በማዕከላዊ የጋዛ ሰርጥ ፈጸመችው በተባለ የአየር ጥቃት 2 ፍልስጤማውያን ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን የሕክምና ምንጮች አስታወቁ። ቱርክ፣ ሳውዲ ዓረቢያና ፓኪስታን በጋራ የመከላከያ ስምምነት ላይ ለመምከር ነገ በኢስታምቡል እንደሚገናኙ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። | |||
| የነሐሴ 23 ቀን 2018 የዓለም ዜና | 29 août 2026 | 00:10:50 | |
በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ ወደ ኢትዮጵያ ሊያቀኑ ነው። የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ በደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያውያን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች የተገደሉበትን ጥቃት አወገዙ። የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ “በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ” ያላቸውን 32 ኤርትራውያን በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ አስታወቀ። ሩሲያ ከኪየቭ አቅራቢያ በሚገኝ መጋዘን ላይ በድሮን በፈጸመችው ጥቃት 37 ሰዎች መገደላቸውን የዩክሬን ባለሥልጣናት ገለጹ። ኔፓልና ቲቤት በሚዋሰኑበት ተራራማ አካባቢ በደረሰው የደራሽ ጎርፍ አደጋ መሞታቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 682 ደረሰ። | |||
| የነሐሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም፤ የዓለም ዜና | 28 août 2026 | 00:13:22 | |
በዛሬው የዓለም ዜና ፤የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለስድስት ወራት ተቋርጦ የነበረውን የሮይተርስ ቋሚ የዜና ወኪል ዘጋቢዎች የሥራ ፈቃድ ማደሱን መግለፁን ፣በደቡብ ሱዳን 49 ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ባለስልጣናት መግለፃቸውን፣ኤስዋቲኒ አወዛጋቢ በሆነ የሶስተኛ ሀገር ስምምነት መሰረት ሁለት ስደተኞችን ከአሜሪካ መቀበሏን፣በሟቹ የኖሮዌ ንጉስ ሀኖርድ አምስተኛ ምትክ ልጃቸው ንጉሥ ሃኮን ስምንተኛ ተብለው መሰየማቸውን ፣ኢራን ከአሜሪካ ጋር ለሚደረግ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ በሩ ጨርሶ አለመዘጋቱን መግለጿን እንዲሁም በኔፓል በደረሰው ከባድ የጎርፍ አደጋ ከ300 በላይ ህንዳውያን የደረሱበት አለመታወቁን አካቷል። | |||
| የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ሐሙስ | 27 août 2026 | 00:12:01 | |
አርስተ ዜና፤ -በያዝነዉ ነሐሴ ወር ብቻ ከ 60 በላይ ኢትዮጵያዉያን ፤ ከዕፅ ዝዉዉር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ከሳዉዲ አረብያ የሚወጡ ዘገባዎች አመላከቱ። -በኔፓል እና በቲቤት ድንበር አካባቢ በተከሰተው አውዳሚ ድንገተኛ የጎርፍ የሟቾች ቁጥር ከ 300 በላይ ደረሰ። ከ 1300 በላይ ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አይታወቅም።-የአሜሪካው 9/11 ወይም የመስከረም 11 ዱ የሽብር ጥቃት ዋና አቀናባሪ ተጠርጣሪ ካሊድ ሼክ መሐመድ ከ20 ዓመት እስራት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ፍርድ ሊቀርብ መሆኑ ተሰማ።-የበቦስኒያ የጦር ወንጀለኛ ጄኔራል ራትኮ ምላዲች በ 84 ዓመታቸዉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። | |||
| የነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና | 26 août 2026 | 00:10:22 | |
የዛሬው የዓለም ዜና የኦባሳንጆን የሰሞኑን የመቀሌ ጉብኝት በበጎ እንደሚመለከተው የአሜሪካ ኤምባሲ መግለፁን፣በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ በትኩረት እና በስጋት እየተመለከቱት መሆኑን መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የምዕራባዉያን ዲፕሎማቶች ማስታወቃቸውን፣የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዝዳንት ከስልጣን መልቀቃቸውን፣አሜሪካ በኢራን ላይ አዲስ የጣለችው የኢኮኖሚ ማዕቀብ ምንም አይነት ግብ አያሳካም ሲሉ የኢራኑ ፕሬዝዳንት መናገራቸውን፣የአሜሪካ የስለላ ኃላፊ ከሩሲያ አቻዎቻቸው ጋር መወያየታቸው ን እንዲሁም በጀርመን አንድ የፍራንክፈርት አውሮፕላን ጣቢያ ሰራተኛ በወባ ህይወቱ ማለፉን አካቷል። | |||
| የነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና | 25 août 2026 | 00:10:37 | |
ደቡብ ሱዳን ፤ ሁለት ኢትዮጵያዊ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪዎች ተገደሉ። የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦባሳንጆ የመቀሌ ድንገተኛ ጉብኝት አደረጉ። ኢትዮጵያ እ.ጎ.አ. በ2028 የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ሰነዷን በይፋ አቀረበች። የግሪክ የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች 79 ስደተኞችን ታደጉ። ዩናይትድ ስቴትስ ዲፕሎማቶቿን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ልትመልስ ነው። 1501ኛው የመውሊድ በዓል ዛሬ ተከበረ። | |||
© My Podcast Data · Independent project · Data from Apple & Spotify