Back

Explore every episode of the podcast ETHIOPIAN PODCASTS

Dive into the complete episode list for ETHIOPIAN PODCASTS . Each episode is cataloged with detailed descriptions, making it easy to find and explore specific topics. Keep track of all episodes from your favorite podcast and never miss a moment of insightful content.

Rows per page:

1–3 of 3

TitlePub. DateDuration
የወንዶች ጉዳይ የዘመን ፌስታል ነው |ረድዔት አሰፋ| hareg podcast11 avr. 202502:03:51


ረድዔት አሰፋ ( Red-8 ) !የሚያስደንቅ ሐሳብና ውበት ባላቸው ግጥሞቹ በማህበራዊ ሚዲያ ይታወቃል ። በግጥሞቹ ውስጥ ሁለንተናውን ዘልቆ የሚያይበት መንገድ ያስገርማል ። ስለሱ ብዙ ማለት ቢቻልም በቆይታ ውስጥ ካነሳቸው ውብ ሐሳቦች ጋር ብንተዋችሁ መርጠናል ። ዛሬ ሐረግ ፖድካስት ረድዔት አሰፋን ከሚያማምሩ ሐሳቦቹ ጋር ከእናንተ ጋር ያቆየዋል ።

እኛ ሀገር ከጦርነት በኃላ የማይድን በሽታ አለ። | ይፍቱስራ ምትኩ | hareg podcast11 avr. 202501:51:15

ይፍቱስራ ምትኩ ከአዲሱ ትውልድ ሴት ፀሐፍት መሐል ቀድመን ከምንጠራቸው ናት ። ሁለት መፅሀፍትን በተወሰኑ አመታት ልዩነት ውስጥ አንባቢዎች ጋር አድርሳለች ። በመፅሀፎቿ የአተራረክ ስልት የቋንቋ አጠቃቀምና ግጥማዊ ባህሪያቸው ከሁሉ ለይተን ይፍቱስራ የጻፈችው ነው ለማለት የሚያስደፍር የራሷን መንገድ እየፈጠረች ነው ። በሁለቱ መፅሀፎቿ ውብ በኾነ መንገድ የማህበረሰብ አረዳድና ስርዓት ፣ ቤተሰብ ፣ ጦርነትና ሌሎች ሐሳቦች ተዳሰዋል ። ከይፍቱስራ ጋር ስነ ፅሁፍና ሴቶች በተመለከቱ ርዕሶች በኩል ስለስራዎቿና ተያያዥ ሐሳቦች ላይ አውግተናል ።

ከሙዓዝ ጀማል ጋር hareg podcast11 avr. 202500:53:21

ሰላም ያ'ገር ሰው


ሙዓዝ ጀማል ቪንቴጅ ፖድካስት የሱ ነው ። ሲትኮሞች ፅፏል ። አሁንም ይፅፋል ። ከ'በስንቱ' ሲትኮም ደራሲዎች መሓልም ሙዓዝ ኣንዱ ነው ። በሓገራችን እየተለመደ በመጣው ስታንድ ኣፕ ኮሜዲ ውስጥ አሻራቸውን ለመተው እየሞከሩ ካሉ ወጣት ስታንድ ኣፕ ኮሜዲያን መሓል ይገኝበታል ። በአንድ የማስታወቂያ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ እየሰራ ከላይ የነገርናችሁ ዘርፎችም ላይ ይሳተፋል ። ብቻ ሌላም ሌላም ። ዛሬ ከእኛ ጋር ያደረገውን ደስ የሚል ጨዋታ ልታዩ ነው ። ከቆይታችን መሓል የተወሰነው ባጋጠመን technical ችግር ጠፍቶብናል ። የምትሰሙት የድምፅ ጥራት ችግርም ኣለ ። ለሁሉም ይቅር በሉን ። እንታረማለን ።


ይመቻችሁ ።


hareg.podcast  

© My Podcast Data · Independent project · Data from Apple & Spotify