Retour

Explorez tous les épisodes du podcast ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ - Connect for Culture Africa - Ethiopia

Plongez dans la liste complète des épisodes de ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ - Connect for Culture Africa - Ethiopia. Chaque épisode est catalogué accompagné de descriptions détaillées, ce qui facilite la recherche et l'exploration de sujets spécifiques. Suivez tous les épisodes de votre podcast préféré et ne manquez aucun contenu pertinent.

Rows per page:

1–6 of 6

TitreDateDurée
Sounds of a Nation: The Ethiopian Music Scene - CfCA - Ethiopia #608 Aug 202501:27:28

ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት | ክፍል 6

ርዕስ፡ የሀገር ድምፅ-የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወግ

እንግዳ፡ ጆርጋ መስፍን - ሳክስፎኒስት፣ሙዚቃ አቀናባሪ

አዘጋጅ፡ ተሾመ ወንድሙ - የሰላም እና ሙዚቃዊ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ

በዚህ የኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ - ኢትዮጵያ ፖድካስት ክፍል የኢትዮጵያን ሙዚቃ ትሩፋት፣የአሁን ተግዳሮቶቹን እንዲሁም ለወደፊት ያለውን ከፍተኛ አቅም እንዳስሳለን፡፡

እንግዳችን ጆርጋ መስፍን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ትሩፋት ላይ በማተኮር ከቅዱስ ያሬድ እስከ ዛሬ ዘመን የሚገኘው ወጣት መር ፈጠራን ይዳስሳል፡፡ ጆርጋ መስፍንና ተሾመ ወንድሙ በጋራ በመሆን እንደ የኦሪጅናል ካሴቶች አለመኖር፣ተገቢ የክምችት ሁኔታ አለመኖር፣ጊዜ ያለፈባቸው ወይም ተደራሽ ያልሆኑ ኮንትራቶች እና ስለባህላዊ መሰረተ ልማት አስፈላጊነት ይዳስሳሉ፡፡

የሚዳሰሱ ርዕሶች ዝርዝር

·         ሙዚቃን ጠብቆ የማቆየት ተግዳሮቶች እና የብሔራዊ ክምትቶች መጥፋት
·         በሙዚቃ ኮንትራቶች እና በቅጂ መብት ጥበቃ የሚያስፈልጉ የህግ መሻሻሎች
·         በወጣቶች የሚመራ ህዳሴ እና እንደ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ያሉ ተቋማት ጠቃሚነት
·         በአገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ቱር ማድረግ
·         የኢትዮጵያ ሙዚቃ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስኬታማ እንዲሆን ለምን ወጥነቱን መጠበቅ እንዳለበት
·         የባህል ዘርፉን የሚገነቡ እንጂ የማያፍኑ ፖሊሲዎችን መገንባት

ይህ ክፍል ፖሊሲ አውጪዎች፣አርቲስቶች፣አስተማሪዎች እና የባህል መሪዎች የኢትዮጵያን ልዩ የሙዚቃ ድምጸት ጠብቀው እንዲያቆዩ እና እንዲለውጡ ጥሪ የሚያቀርብ ነው፡፡

 
🎙️ Connect for Culture Africa – Ethiopia Podcast | Episode 6
Title: “Sounds of a Nation: The Ethiopian Music Scene”
👤 Guest: Jorga Mesfin – Saxophonist, Composer
🎤 Host: Teshome Wondimu – Founder & Executive Director, Selam

In this powerful episode of Connect for Culture Africa – Ethiopia Podcast, we explore the state of Ethiopian music—its legacy, its current struggles, and its immense future potential.

Our guest, Jorga Mesfin, reflects on the rich musical heritage of Ethiopia, from the time of Saint Yared to today's youth-led innovation. Together with host Teshome Wondimu, they unpack urgent issues: the loss of original cassettes, the lack of proper archiving, outdated or inaccessible music contracts, and the need for strong cultural infrastructure.

🎶 Topics discussed include:

The crisis of music preservation and the loss of national archives
Legal reforms needed in music contracts and copyright protection
Youth-driven revival and the importance of institutions like Yared Music School
Touring locally vs. internationally
Why Ethiopian music should maintain its authenticity for global success
Building policies that support—not stifle—the cultural sector
This episode is a call to action for policymakers, artists, educators, and cultural leaders to unite in preserving and evolving Ethiopia’s sonic identity.

The Reel Story: A Conversation on Ethiopia’s Film - CfCA Ethiopia #518 Jul 202501:15:12

በኢትዮጵያ ፊልም ዙሪያ ያተኮረ ውይይት| ሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት - ምእራፍ 2

ወደ ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ (ሲኤፍሲኤ) ኢትዮጵያ ፖድካስት እንኳን በደህና መጡ፤ በዚህ ክፍል በባህል እና በዘላቂ ልማት መካከል ያለውን ቁልፍ ግንኙነት እንዳስሳለን፡፡

በዚህ በኢትዮጵያ ፊልም ዙሪያ ያተኮረ ውይይት ላይ ከዝነኛው ፊልም አዘጋጅ ሄኖክ አየለ እንዲሁም ተሾመ ወንድሙ ጋር የኢትዮጵያ ፊልም ዘርፍ ላይ ወቅታዊ እና ግልጽ ውይይት እናደርጋለን፡፡

በዚህ ክፍል የሚከተሉትን ቁልፍ ጥያቄዎችን እናነሳለን፡

  • የኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስትሪ እንደ ኔትፍሊክስ ላሉ ዓለም አቀፍ መተግበሪያዎች ዝግጁ ነው?

  • የፊልም ትምህርትን፣የገንዘብ ድጋፍን እና የፖሊሲ ትግበራን ወደ ኋላ እየጎተተው የሚገኘው ምንድነው?

  • በፍጥነት እየተቀያየረ በሚገኝ ዲጂታል ዓለም ላይ የቅጂ መብት እንዴት ሊከበር ይችላል?

  • በባህል ልማት ውስጥ መንግስት እና ኢንቬስተሮች ምን አይነት ሚና መጫወት አለባቸው?

ከሲኒማ አዳራሾች የመጥፋት  ሁኔታ አንስቶ እስከ በወጣቶች ስለሚመራ ፈጠራ እና የአገር ውስጥ የስርጭት አማራጮች በመዳሰስ- በዚህ ክፍል የኢትዮጵያ ፊልም ዘርፍ የት ጋር እንዳለ እና ቀጥሎም ወደ የት መሄድ እንዳለበት እንመለከታለን፡፡

በአፍሪካ ባህል ላይ የተሻለ ኢንቨስትመንት እንዲኖር የምንጠይቅበትን ይህን ክፍል ይመልከቱ፣ያጋሩ እንዲሁም ቻናሉን ሰብስክራይብ ያድርጉ፡፡ ይህ ክፍል በስፖቲፋይ እና አፕል ፖድካስት ላይም ይገኛል፡፡

Connect with us: https://cfcafrica.org https://www.facebook.com/CFCA23 https://www.instagram.com/cfcafrica https://www.linkedin.com/company/connectforcultureafrica/posts/?feedView=all https://x.com/cfcaafrica

Culture as a Catalyst for Peace, Rights, and Democracy - CfCA Ethiopia #427 Jun 202500:55:29

ክፍል 3፡ የባህል ሚና ለሰላም, ሰብዓዊ መብት እና ዲሞክራሲ ግንባታ

በዚህ ክፍል የባህል ተመራማሪ ከሆኑ ዶ/ር ጥላሁን በጅቷል ጋር ኪነ-ጥበብ፣ባህል እና ፈጠራ በሰላም ግንባታ፣ሕብረተሰብ ላይ ተሃድሶ በመፍጠር እንዲሁም በብሔራዊ ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ምን አይነት ሚና እንደሚጫወቱ እንዳስሳለን፡፡

ከባህላዊ ትሩፋቶች እስከ ዘመናዊ ኪነ-ጥበብ ድረስ ያሉትን ሁኔታዎች እንዲሁም በባህል፣በግጭት መፍታት እና በሰብዓዊ መብት መካከል ያሉትን ጥልቅ ትስስሮች ዶ/ር ጥላሁን ይተነትናሉ፡፡ በተጨማሪም የበርካታ አመታት ጥናት ላይ ተመርኩዘው ዶ/ር ጥላሁን የሚከተሉት ላይ ምልከታቸውን ያጋራሉ፡፡

·         ከበፊት የተወረሱ፣ጎልተው የሚታዩ እንዲሁም ብቅ ብቅ እያሉ የሚገኙ አዳዲስ ባህሎች ሚና
·         ባህል በምን መልኩ የማኅበራዊ ስምምነትን ያዳብራል
·         የኢትዮጵያን የፈጠራ ዘርፍ ምን ተግዳሮቶች ተጋርጠውበታል
·         ኪነ-ጥበብ ለምን የፖሊሲ ድጋፍ እና የኢኮኖሚ ኢንቨስትመንት ያስፈልገዋል

ይመልከቱ እንዲሁም አስተያየትዎን ያስፍሩ!

ሰብስክራይብ ያድርጉ፤ አዳዲስ ክፍሎች ሲወጡ እንዲደርስዎም የደወል ምልክቱን ይጫኑ!

ለበለጠ መረጃ ድረ-ገጻችንን https://cfcafrica.org ይጎብኙ፡፡ 

In this powerful episode, we sit down with Dr. Tilahun Bejitual—a cultural researcher—to explore how art, culture, and creativity can play a transformative role in peace building, social healing, and national identity in Ethiopia.

Drawing from years of research and fieldwork, he shares insight on: 

• The role of residual, dominant, and emerging cultures
• How culture can foster social harmony
• The challenges facing Ethiopia’s creative sector
• Why the arts need policy support and economic investment

Watch, comment, and share your thoughts below.

Don’t forget to subscribe and hit the notification bell to stay updated.

Discover more at https://cfcafrica.org.

#CfCAEthiopia #1PercentForCulture #SustainablePublicFunding

Culture as a Driver for Job Creation - CfCA Ethiopia #306 Jun 202500:58:30
ባህል እና የባህል እና ፈጠራ ኢንዱስትሪው ላይ ለካበተ እና ጥልቅ ውይይት መድረክ በሆነው የሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት 3ኛ ክፍል ባህል ለስራ እድል ፈጠራ ያለው ሚና የሚል ውይይት ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ በተሾመ ወንድሙ ተዘጋጅቶ የሚቀርበው እና የእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ያለው ይህ ክፍል በባህል እና በስራ ቅጥር መካከል ያለውን ወሳኝ ሚና ይዳስሳል፡፡የባህል ትሩፋት የዘላቂ ስራ እና የኢኮኖሚ እድገት ምንጭ ሊሆን ይችላል? በውይይቱ የሚዳሰስ ጉዳይ ነው፡፡
ውይይቱ የኢትዮጵያን ባህል፣አፈ-ታሪክ እንዲሁም ሕብረተሰብ በማጥናት የአራት አስርት አመታት ልምድ ያላቸው ዶ/ር ባይለየኝ ጣሰው እንግዳ በመሆን የቀረቡበት ሲሆን ከተሾመ ወንድሙ ጋር በመሆን የኢትዮጵያ የባህል እሴቶች የስራ ፈጠራን፣አገር በቀል ኢኮኖሚን ለማነሳሳት እንዲሁም ማኅበረሰቦችን ለማብቃት ያላቸውን አቅም ይፈትሻሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ ድረ-ገጻችንን https://cfcafrica.org ይጎብኙ፡፡

Culture as a Driver for Job Creation is the third episode in the CfCA Ethiopia Podcast series-a platform for rich and reflective conversations on culture and the cultural and creative industries (CCIs). Hosted by Teshome Wondimu and subtitled in English, this episode explores the vital link between culture and employment in Ethiopia. Can cultural heritage become a source of sustainable jobs and economic development?

Joining the discussion is Dr. Bayleyegn Tasew, a renowned cultural anthropologist with nearly four decades of experience studying Ethiopian culture, folklore, and society. Together, they unpack the potential of Ethiopia’s cultural assets to drive job creation, stimulate local economies, and empower communities.

Discover more at https://cfcafrica.org.

Public Funding for the Culture and Creative Sector in Ethiopia - CfCA Ethiopia #216 May 202500:55:55

የሲኤፍሲኤ ኢትዮጵያ ፖድካስት ሁለተኛው ክፍል  ‘የመንግስት ድጋፍ ለባህል’ የሚል ሲሆን- በባህል እና የባህል እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ላይ የካበቱ እና ጥልቀት ያላቸው ውይይቶች የሚካሄዱበት መድረክ ነው፡፡

በተሾመ ወንድሙ ተዘጋጅቶ ከእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ጋር የሚቀርበው ይህ ክፍል በኢትዮጵያ እንዲሁም ከዛም ባሻገር ኪነ-ጥበብን ለመደገፍ የመንግስት ድጋፍ እንዴት እንደሚመደብ ይዳስሳል፡፡በባህል ላይ የመንግስት ኢንቨስትመንት ምን ይመስላል? ተስፋ ሰጪ የሆኑ አዳዲስ ክንውንኖች ምንድን ናቸው፤ክፍተቶችስ ያሉት እምን ጋ ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች ይመለከታል፡፡

ይህንን ውይይት የሚቀላቀሉት ዶ/ር ይስማ ጽጌ ሲሆኑ ጥናታዊ ምርምር ስራዎችን የሚሰሩት ዶ/ር ይስማ በቅርብ ጊዜ የሰሩት ጥናት በባህል ዘርፉ ላይ የመንግስት የገንዘብ ድጋፍ ምን ይመስላል የሚለው ላይ የብርሃን ጮራን የሚፈነጥቅ ነው፡፡ አቶ ተሾመ እና ዶ/ር ይስማ በጋራ የዚህን ጥናት መረጃ በጥልቀት ይመለከታሉ፣ዘላቂ የገንዘብ ድጋፍ እንዳይኖር የሚያደርጉ እንቅፋቶች እንዲሁም የለውጥ መንገዶችም ላይ ይወያያሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ https://cfcafrica.org

 

Public Funding for Culture is the second episode in the CfCA Ethiopia Podcast series—a platform for rich and reflective conversations on culture and the cultural and creative industries (CCIs).

Hosted by Teshome Wondimu and subtitled in English, this episode explores how public funds are allocated to support the arts in Ethiopia and beyond. What does government investment in culture look like? What are the promising developments—and where do the gaps remain?

Joining the conversation is Dr. Yisma Tsige, a researcher whose recent work shines a light on public financing within the cultural sector. Together, they delve into the data, discuss the barriers to sustainable funding, and highlight pathways for progress.

Tune in and explore more at https://cfcafrica.org

Defining Culture and Its Importance - Firehiwot Bayu (PhD) - CfCA Ethiopia #125 Apr 202500:54:43

የባህል ምንነት እና ፋይዳው የሚለው የመጀመሪያ ክፍል የፖድካስት ዝግጅት የሲኤፍሲኤ ፖድካስት ተከታታይ ክፍሎችን መክፈቻ ዝግጅት ሲሆን ይህ ፖድካስት በባህል እና በባህላዊ እና ፈጠራ ኢንዱስትሪው ላይ ላተኮሩ የካበቱ እንዲሁም ጥልቅ ምልከታን የያዙ ውይይቶች የሚንጸባረቁበት መድረክ ነው፡፡

በዚህ በተሾመ ወንድሙ አቅራቢነት በሚቀርበው እና የእንግሊዝኛ የግርጌ መግለጫ ባለው የመክፈቻ ክፍል ‘ባህል ምንድነው? ፋይዳውስ?ኅብረሰተብን በመቅረጽ ረገድ ምን ሚና ይጫወታል? እና በባህል ጥላ ስር የሚገኙት ዘርፎች ምንድናቸው?’ የሚሉ መሰረታዊ ጥያቄዎችን በማንሳት መድረኩን እንከፍታለን፡፡

ዶ/ር ፍሬሕይወት ባዩ በምልከታቸው ባህል በእለት ተእለት ሕይወታችን እንዲሁም በማኅበረሰብ ላይ ያለውን ትርጉም እና አንድምታ በዝርዝር እንድመለከት በማድረግ ለውይይቱ ጥልቀት እና ትርጉም ይሰጡልናል፡፡

የበለጠ ለማወቅ የሚከተለውን ድረ-ገጽ ይጎብኙ https://cfcafrica.org

 

Defining Culture and Its Importance launches the CfCA Ethiopia Podcast series—a platform for rich and reflective conversations on culture and the cultural and creative industries (CCIs). In this opening episode, hosted by Teshome Wondimu, subtitled in English, we set the stage with fundamental questions: What is culture? Why does it matter? What role does it play in shaping society? and What domains fall under the umbrella of culture? Bringing depth and nuance to the conversation is Dr. Firehiwot Bayu, whose insights help us unpack the meaning and impact of culture in our everyday lives and communities.

Tune in and explore more at https://cfcafrica.org

© My Podcast Data · Projet indépendant · Données issues d'Apple & Spotify