Explorez tous les épisodes du podcast Evangelist Elsabet Tasisa
| Titre | Date | Durée | |
|---|---|---|---|
| ይህ አይሆንልኝም | 02 Mar 2025 | 00:11:45 | |
አንደኛ መጽሐፈ ሳሙኤል 2:30 [30] ስለዚህም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእውነት ቤትህ የአባትህም ቤት ለዘላለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፥ አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ አይሆንልኝም። | |||
| አካሔዳችሁ ከጌታ ጋር እንዴት ነው ? | 01 Mar 2025 | 00:07:19 | |
ኦሪት ዘፍጥረት 5:24 [24] ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና። | |||
| ለእግዚአብሔር መገኘት | 28 Feb 2025 | 00:08:40 | |
1 ሳሙኤል 3:3-4 [3] ሳሙኤልም ደግሞ የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ የእግዚአብሔር መብራትም ገና አልጠፋም ነበር። [4] እግዚአብሔርም ሳሙኤልን ጠራው። ሳሙኤልም፣ “እነሆኝ” አለ፤ | |||
| የኢየሱስ ደም ባለስልጣን ነው። | 27 Feb 2025 | 00:10:27 | |
1 ዮሐንስ 1:7 [7] ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ፣ እኛም በብርሃን ብንመላለስ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፤ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኀጢአት ሁሉ ያነጻናል። | |||
| የዘኬዎስ እምነት / betty yeneneh | 25 Feb 2025 | 00:08:49 | |
ሉቃስ 19:2-5 [2] ስሙ ዘኬዎስ የተባለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፤ ዋና ቀረጥ ሰብሳቢና ሀብታም ነበረ። [3] እርሱም ኢየሱስ የተባለው የትኛው እንደ ሆነ ሊያይ ይፈልግ ነበር፤ ቁመቱ ዐጭር ነበረና ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ሊያየው አልቻለም። [4] ኢየሱስ በዚያ መንገድ ያልፍ ስለ ነበርም፣ ሊያየው ወደ ፊት ሮጦ አንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ። [5] ኢየሱስም እዚያ ቦታ ሲደርስ፣ ቀና ብሎ፣ “ዘኬዎስ ሆይ፤ ዛሬ አንተ ቤት መዋል ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ” አለው። | |||
| በመጠን እንኑር | 24 Feb 2025 | 00:09:16 | |
1 ተሰሎንቄ ሰዎች 5:5-8 [5] ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም፤ [6] እንግዲያስ እንንቃ በመጠንም እንኑር እንጂ እንደ ሌሎች አናንቀላፋ። [7] የሚያንቀላፉ በሌሊት ያንቀላፋሉና፥ የሚሰክሩም በሌሊት ይሰክራሉና፤ [8] እኛ ግን ከቀን ስለ ሆንን፥ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እየለበስን በመጠን እንኑር፤ | |||
| የወንጌል ሀይል እና የስብእና ለውጥ በአናሲሞስ ህይወት በወፍ በረር ሲቃኝ | 23 Feb 2025 | 00:08:24 | |
ፊልሞና 1:10-11 [10] በእስር እያለሁ ስለ ወለድሁት ልጄ ስለ አናሲሞስ እለምንሃለሁ። [11] አስቀድሞ የሚጠቅምህ አልነበረም፤ አሁን ግን ለአንተም ሆነ ለእኔ የሚጠቅም ሰው ሆኗል። | |||
| ልባም መሆን | 22 Feb 2025 | 00:08:52 | |
ምሳሌ 31:10-18 [10] ጠባየ መልካምን ሚስት ማን ያገኛታል? ከቀይ ዕንእጅግ ትበልጣለች። [11] ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል፤ የሚጐድልበትም ነገር የለም። [12] በሕይወት ዘመኗ ሁሉ፣ መልካም ታደርግለታለች እንጂ አትጐዳውም። [13] የበግ ጠጕርና የተልባ እግር መርጣ፣ ሥራ በሚወዱ እጆቿ ትፈትላቸዋለች። [14] እንደ ንግድ መርከብ፣ ምግቧን ከሩቅ ትሰበስባለች። [15] ገና ሳይነጋ ትነሣለች፤ ለቤተ ሰቧ ምግብ፣ ለሴት አገልጋዮቿም ድርሻቸውን ትሰጣለች። [16] ራሷ አስባ የዕርሻ መሬት ትገዛለች፤ በምታገኘውም ገንዘብ ወይን ትተክላለች። [17] ብርታትን ታጥቃ ሥራዋን ታከናውናለች፤ ክንዶቿም ለሥራ ብርቱ ናቸው። [18] ሥራዋ ትርፋማ መሆኑን ታስተውላለች፤ በሌሊትም መብራቷ አይጠፋም። | |||
| የእግዚአብሔርን እቃ ጦር ሁሉ ልበሱ | 21 Feb 2025 | 00:08:02 | |
ኤፌሶን 6:10-18 [10] በተረፈ በጌታና ብርቱ በሆነው ኀይሉ ጠንክሩ። [11] የዲያብሎስን የተንኰል ሥራ መቋቋም ትችሉ ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ ልበሱ። [12] ምክንያቱም ተጋድሏችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች፣ ከሥልጣናትና ከኀይላት እንዲሁም በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከርኩሳን መናፍስት ሰራዊት ጋር ነው። [13] ክፉው ቀን ሲመጣ መቋቋም ትችሉ ዘንድ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ ልበሱ፤ ሁሉን ከፈጸማችሁ በኋላ ጸንታችሁ መቆም ትችላላችሁና። [14] እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ዝናር ታጥቃችሁ፣ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፣ [15] በሰላም ወንጌል ዝግጁነት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ። [16] ከእነዚህም ሁሉ ጋር፣ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ [17] የመዳንን ራስ ቍር አድርጉ፤ የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። [18] በሁሉ ዐይነት ጸሎትና ልመና፣ በማንኛውም ሁኔታ በመንፈስ ጸልዩ፤ ይህንም በማሰብ ንቁ፤ ስለ ቅዱሳንም ሁሉ በትጋት ልመና አቅርቡ። | |||
| ድርሻችንን እንወጣ | 18 Feb 2025 | 00:09:29 | |
ዘፀአት 23:25 [25] አምላክህን እግዚአብሔርን (ኤሎሂም) አምልክ፤ በረከቱም በምትበላውና በምትጠጣው ላይ ይሆናል፤ በሽታንም ከአንተ ዘንድ አርቃለሁ። | |||
| የተወደድን የእግዚአብሔር ልጆች ሆይ | 17 Feb 2025 | 00:07:36 | |
ኤፌሶን 5:1-2 [1] እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን ምሰሉ፤ [2] ክርስቶስ እንደ ወደደን ራሱንም ስለ እኛ መልካም መዐዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር እንደ ሰጠ እናንተም በፍቅር ተመላለሱ። | |||
| ባዶ አትሁኑ | 16 Feb 2025 | 00:11:51 | |
ኤፌሶን 5:15-18 [15] እንግዲህ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንደ ጥበበኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ። [16] ቀኖቹ ክፉ ናቸውና ዘመኑን በሚገባ ዋጁ። [17] ስለዚህ ሞኞች አትሁኑ፤ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ። [18] በመንፈስ ተሞሉ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ፤ ይህ ብክነት ነውና። | |||
| መንፈሳዊ ስፍራን አለመልቀቅ / Hermon | 16 Feb 2025 | 00:11:41 | |
ሉቃስ 24:14-17 [14] እነርሱም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርስ ይነጋገሩ ነበር። [15] እየተነጋገሩና እየተወያዩ ሳሉም ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ጀመር፤ [16] ነገር ግን እንዳያውቁት ዐይናቸው ተይዞ ነበር። [17] እርሱም፣ “እየሄዳችሁ፣ መንገድ ላይ እርስ በርስ እንዲህ የምትወያዩት ምንድን ነው?” አላቸው። እነርሱም በሐዘን ክው ብለው ቆሙ። | |||
| እንድትሰማ ጩህ / Yemiserach Dawit | 10 Feb 2025 | 00:07:58 | |
ሉቃስ 18:38 [38] እርሱም፣ “የዳዊት ልጅ፣ ኢየሱስ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ ጮኸ። | |||
| የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ | 09 Feb 2025 | 00:07:35 | |
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1:18-19 [18-19] ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ | |||
| እኛ የሰማይ ወኪሎች ነን | 08 Feb 2025 | 00:10:15 | |
የሉቃስ ወንጌል 4:17-19 [17-19] የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ፦ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ። | |||
| ኢየሱስ ፍፁም ሰላም ነው / Betty Yenenh | 07 Feb 2025 | 00:08:37 | |
ኦሪት ዘፍጥረት 39:1-2 [1] ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ፤ የፈርዖን ጃንደረባ የዘበኞቹም አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ዺጥፋራ ወደ ግብፅ ካወረዱት ከእስማኤላዉያን እጅ ገዛው። [2] እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፥ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ በግብፃዊው ጌታውም ቤት ነበረ። | |||
| የእግዚአብሔር አብሮነት / Azeb Hailu | 06 Feb 2025 | 00:10:31 | |
ኦሪት ዘፍጥረት 39:1-2 [1] ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ፤ የፈርዖን ጃንደረባ የዘበኞቹም አለቃ የሚሆን የግብፅ ሰው ዺጥፋራ ወደ ግብፅ ካወረዱት ከእስማኤላዉያን እጅ ገዛው። [2] እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፥ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ በግብፃዊው ጌታውም ቤት ነበረ። | |||
| ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና / Yemiserach Dwit | 06 Feb 2025 | 00:07:35 | |
ወደ ቲቶ 2:11-13 [11] ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ [12-13] ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ | |||
| የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ | 05 Feb 2025 | 00:06:12 | |
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1:18-19 [18-19] ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ | |||
| አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል። | 04 Feb 2025 | 00:08:24 | |
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:19 አማ54 [19] አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል። | |||
| በሕይወት እንድንኖር በፍጹም ልባችን በፍፁም ነፍሳችን እግዚአብሔርን እንውደድ | 02 Feb 2025 | 00:08:36 | |
በሕይወት እንድንኖር በፍጹም ልባችን በፍፁም ነፍሳችን እግዚአብሔርን እንውደድ ኦሪት ዘዳግም 30:6 [6] በሕይወትም እንድትኖር፥ አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ እንድትወድድ አምላክህ እግዚአብሔር ልብህን የዘርህንም ልብ ይገርዛል። | |||
| እንገኝ ! ይገኝልናል ። በእግዚአብሔር ፊት ፀንተን እንቁም | 02 Feb 2025 | 00:15:03 | |
ትንቢተ ዕንባቆም 2:1 [1] በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፥ የሚናገረኝንም፥ ስለ ክርክሬም የምመልሰውን አውቅ ዘንድ እመለከታለሁ። | |||
| እናንተ የእግዚአብሔር ምርጦች ሆይ ፍቅርን ልበሱ | 02 Feb 2025 | 00:07:42 | |
ቈላስይስ 3:12-14 [12] እንግዲህ የተቀደሳችሁና የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ምርጦች እንደ መሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ጨዋነትንና ትዕግሥትን ልበሱ፤ [13] እርስ በርሳችሁ ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ጌታ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ሌላውን ይቅር በሉ። [14] በእነዚህ ሁሉ ላይ ሁሉን በፍጹም አንድነት የሚያስተሳስረውን ፍቅርን ልበሱት። | |||
| ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል ማነው? | 01 Feb 2025 | 00:11:00 | |
ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል ማነው? ዘመን እየተጠናቀቀ በመጣ ቁጥር ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚሞክር ነገርች እየጨመረ እንደሚመጡ ግልፅ ነው። እኛ ግን በወደደን በክርስቶስ በዚህ ታላቅ ፍቅር ውስጥ ተሰውረን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካገኘነው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን የሚችል ምንም ነገር እንደሌለ እርግጠኛ ነኝ። ወደ ሮም ሰዎች 8:35 [35] ከክርስቶስ ፍቅር ሊለየን የሚችል ማነው? ችግር ወይስ መከራ? ስደት፥ ወይስ ራብ? ወይስ ራቊትነት፥ ወይስ አደጋ? ወይስ ሰይፍ? | |||
| እየጸለየም ሳለ ሰማይ ተከፈተ | 01 Feb 2025 | 00:09:21 | |
ሕዝቡ ሁሉ ከተጠመቀ በኋላ ኢየሱስም ተጠመቀ፤ እየጸለየም ሳለ ሰማይ ተከፈተ፤ Now, when all the people were baptized, Jesus was also baptized, and while He was praying, the [visible] heaven was opened,d | |||
| እኔ ለክርስቶስ ሞቻለሁ እናንተስ ? | 01 Feb 2025 | 00:08:17 | |
ወደ ገላትያ ሰዎች 2:20 [20] ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው። | |||
| As was His custom on the Sabbath day. And He stood up to read. | 28 Jan 2025 | 00:12:10 | |
የሉቃስ ወንጌል 4:16 አማ54 [16] ወዳደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ፥ ሊያነብም ተነሣ። ልማዳችን ኢየሱስ ልማዳችን ፀሎት ልማዳችን ህልውናው ልማዳችን የእግዚአብሔር ቃል ማንበብ ማሰላሰል ''ልማዳችን በክርስቶስ የህይወት ስርአት ውስጥ የመመላለስ ህግ ነው። | |||