Explorez tous les épisodes du podcast እናትHood | EnatHood
| Titre | Date | Durée | |
|---|---|---|---|
| Motherhood, working in health care, marriage and spiritual life with Dr. Betelehem Asnake | 22 Apr 2026 | 00:59:00 | |
Dr. Betelehem M. Asnake, MD is a board certified Anesthesiologiest. She is also global health director at the University of California Los Angeles. She is a founder and manager of Mulu Mentor, which help underrepresented and disadvantaged pre-medical students navigate the medical school application process through targeted mentorship. Dr. Betelehem M. Asnake is a wife and a mom of three children. On this episode, she shares how she manages motherhood, work and relationship together with her spiritual life. Check out Dr. Beti’s site at https://theanesthesiologistmom.com/ Instagram - https://www.instagram.com/dr.beti?igsh=MmR6b3ZwdXZwMndy TikTok - https://www.tiktok.com/@dr.beti?_r=1&_t=ZP-95k0Ikg95aw | |||
| ምግብ መራጭ ልጆችን ለማገዝ | How to help picky eaters ከብሩክታይት ወልደማርያም MPH, CLE, ICCE,CWC #enathood #habesha | 31 Mar 2026 | 00:47:19 | |
In this episode, we discuss what picky eating is and what we can do to help kids eat variety of foods. Beruktawet Woldemariam(MPH), a mom of two and a professional with extensive experience in maternal and children health. https://mydoctor.kaiserpermanente.org/ncal/providers/beruktawetwoldemariam https://www.instagram.com/itsbrook_?igsh=MWptdTR2Yzg1Mjdleg== | |||
| Parenting with Purpose with Helina Girma - ወላጅነትን በአላማ ከህሊና ግርማ ጋር | 17 Mar 2026 | 01:01:10 | |
Helina Girma is an International Leadership Trainer, Public Speaker, and a Life Coach. She began her career as a Medical Technologist after she earned her Bachelors in Biomedical Sciences. Helina is author of a weekly reflection journal called Parenting with Purpose. It intends to guide parents through intentional reflection on their parenting journey. Parenting with Purpose journal: https://amzn.to/4bobnvg Website: [https://www.insideouttransform.com/](https://www.insideouttransform.com/helina) Instagram: https://www.instagram.com/helina_insideout?igsh=dHJnemFyY3B2amcz | |||
| የልጆች ቁጥር ላይ በእርግዝና ጊዜ የሚሰጡ አስተያየቶች - Opinions about number of children | 28 Feb 2025 | 00:14:47 | |
In this episode of the EnatHood podcast, I shared and discussed the opinions and comments I received regarding my fourth pregnancy, family size, and related topics. Read the EnatHood blog here: https://enathood.com/ Download a free hospital bag checklist here: https://artisanal-thinker-4913.ck.page/6ab4fb3db3 Use the promo code ENATHOOD to get a 10% discount on the Fidel Sound Amharic book here: https://fideltrading.com/ #enathood #እናትHood #habeshapodcast #ethiopian #እናት #habesha #habeshachewata #ethiopiancommunity #pregnancyjourney #pregnancyannouncement #familysize #bigfamily | |||
| የእናቶች እና የልጆች ጤና ከብሩክታይት ወልደማርያም የህዝብ ጤና ባለሙያ ፣ የወሊድ እና የጡት ማጥባት አስተማሪ Maternal and Children Health | 21 Feb 2025 | 00:59:32 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከብሩክታይት ወልደማርያም ጋር ስለ እናቶች እና ጨቅላ ህፃናት ጤና ፣ ስለወሊድ፣ ስለ ግል ኑሮ እና ትምህርት ፣ ህክምና በአሜሪካ እና እናትነት ተጨዋውተናል። እንደምትደሰቱበት እርግጠኛ ነኝ። መልካም ቆይታ። ብሩክታይት ለማግኘት ፦ https://mydoctor.kaiserpermanente.org/ncal/providers/beruktawetwoldemariam የብሩክታይት IG :- https://www.instagram.com/itsbrook_?igsh=MWptdTR2Yzg1Mjdleg== Maternal and Children Health with Beruktawet Woldemariam, MPH, CLE, ICCE, CWC In this powerful episode, we discuss the vital importance of educating ourselves and advocating for our rights within the healthcare system, particularly as Black individuals facing significant disparities. Beruktawet Woldemariam, a mom of two and a professional with extensive experience in maternal and child health, shares her personal journey, including her experiences with two cesarean births. Her insights shed light on the challenges and triumphs of navigating healthcare as a Black mother, emphasizing the need for awareness, support, and empowerment. Tune in for an enlightening conversation that highlights the importance of advocacy in creating equitable health outcomes for all families! | |||
| እናትHood ፓድካስት ተመልሷል - EnatHoood podcast is back! | 18 Feb 2025 | 00:17:19 | |
EnatHood Podcast is Back! I’m Back! A New Chapter Begins. After a long break, I’m excited to reconnect with all of you! In this episode, I share my journey during my time away, what I’ve learned, and the inspiration fueling my return. Get ready for fresh content, exciting stories, and a glimpse into what the future holds. I can't wait to dive back in and share more with you all. Let’s embark on this new adventure together! Tune in and let's catch up! 🌟 Read EnatHood blog : https://enathood.com/ Download free hospital bag checklist https://artisanal-thinker-4913.ck.page/6ab4fb3db3 Use ENATHOOD promo code for 10% discount to buy Fidel sound Amharic book https://fideltrading.com/ #enathood #እናትHood #habeshapodcast #ethiopian #እናት #habesha #habeshachewata | |||
| የአራት ልጆች እናት ፣ የተሸላሚ የልጆች መፅሀፍ ፀሐፊ ፣ የሳይበር ደህንነት ኢንጂነር ከዘኒት ከማል | Zinet Kemal children book author | 27 Jun 2024 | 01:04:58 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ከዘኒት ከማል ጋር ስለ እናትነት ጉዞዋ ፣ ስለ ፃፈቻቸው አራት መፅሀፎች ፣ ስለ ስራዋ ፣ ኑሮ በሚኒሶታ አሜሪካ ከአራት ልጆች ጋር ፣ ስለ ዘጠኝ አመት እስከ ማስተርስ የትምህርት ጉዞዋ ፣ ስለ ስኬት ሚስጥሯ ጨምሮ በስራዋ ስለተሸለመቻቸው ለመዘርዘር ከሚያዳግቱ ብዙ ሽልማቶቿ እና ሌሎችም በጣም ጠቃሚ ነገሮች ተነጋግረናል። እንደምትደሰቱበት እርግጠኛ ነኝ።
መልካም ቆይታ።
Zinet Kemal is a mother of four, a multi-award winning cybersecurity advocate and a four times best-selling author.
She is currently working as Cloud Security Engineer at Best Buy and Board member at a non-profit, Black Girls in Cyber.
She is a Georgia Tech University graduate with a Masters of Science degree in Cybersecurity. She earned a B.S. degree in Computer Science and LLB degree in Law.
She wrote award-winning children's books, including "Proud in Her Hijab", "Oh, No ... Hacked Again!” and "See Yourself in Cybersecurity" promote empowerment, online safety and cyber careers for children.
Zinet is a Tedx speaker, LinkedIn instructor, top 25 cybersecurity leader, also recognized as 2023 Minneapolis/St. Paul Business Journal 40 under 40. She has been featured in various media outlets including Good Morning America, 11Alive, BBC and CBS Minnesota - WCCO, ABC News, Yahoo News, AFROTECH and ebs.
Website https://zinetkemal.com/
IG : https://www.instagram.com/zinet_kemal
| |||
| የወላጅነት ጉዞ ከኦቲዝም ጋር ፤ የመልካም አባት ተምሳሌት ቢኒያም ንጉሴ #ethiopian #fatherlove #autism #enathood | 17 Jun 2024 | 01:03:10 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከወትሮ በተለየ የአባቶችን ታሪክ ይዘን መጥተናል።
የመልካም አባት ተምሳሌት የሆነው ቢንያም ንጉሴ የወላጅነት የአባትነት ጉዞውን ፥ እና የሶስተኛ ልጁን ታሪክ ፥ ከኦቲዝም ጋር ተያይዞ የገጠመውን ውጣ ውረድ ፥ የተጠቀመበትን እና የረዳውን ሁሉ ነገር በሰፊው አጫውቶናል።
ቢኒያም የሶስት ልጆች አባት ሲሆን ለልጆቹ በጣም ቅርብ እና በለት ተለት ኑሮአቸው ከፍተኛ ተሳትፎ የሚያደርግ አባት ነው። በተለይም ለሶስተኛ ልጁ በሚያደርገው በትጋት የተሞላ ክትተል የኦቲዝም ልዮ ፍላጎት ቢኖረው በጥሩ መሻሻሎችን እንዲያመጣ ሊረዳው ችሏል።
👉🏾 ቢኒያም ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@benyam77?_t=8nFob0z7gmE&_r=1
#habesha #ኢትዮጵያ #እናት #habeshatiktok #autismlife #autismawareness #ethiopian #fathersday
| |||
| የሳይበር ደህንነት (cybersecurity) ለራሳችን እና ለልጆቻችን ከሳይበር ደህንነት ባለሙያ ከሁስኒ አወል ጋር | 31 May 2024 | 00:40:32 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የሳይበር ደህንነት (cybersecurity) ኢንጅነር እና አማካሪ ከሆነው ሁስኒ አወል ጋር የራሳችን እና የልጆቻችንን የሳይበር ደህንነት እንዴት እንደምንጠብቅ ተነጋግረናል። ጠቃሚ መረጃዎች እንደምታገኙበት እርግጠኛ ነኝ።
መልካም ቆይታ።
ሁስኒ አወል የሳይበር ደህንነት (cybersecurity) ኢንጅነር እና አማካሪ ነው። በአሁን ጊዜ ለToyota Financial Services በአማካሪነት እየሰራ ይገኛል። በኢትዮጵያ በግል እና የመንግስት የሳይበር ደህንነት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ለማህበረሰባችን በሙያው አገልግሎት ይሰጣል።
#amharic #ethiopia #ethiopian #cybersecurity #enat #enathood
| |||
| ከAyla’s የልጆች መጫወቻ እና መማሪያ አዘጋጅ ሳራ ሱከር Ayla’s Kids Learning Tools with Sara Suker #የልጆች #ኢትዮጵያ #እናት | 14 May 2024 | 00:40:32 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ከሳራ ሱከር ጋር ስለ እናትነት ጉዞዋና ለልጆች መጫወቻ እና መማሪያ ስለምታዘጋጃቸው ነገሮች ፣ ስለ ቢዝነስ እና ሌሎችም ነገሮች ተነጋግረናል። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት እርግጠኛ ነኝ።
ሳራ የሁለት ልጆች እናት ናት። በቅርቡ የሙሉ ጊዜ ስራዋን በቤት ከልጆችዋ ጋር ለመሆን ወስና በቤት ቤተሰቧን እየተንከባከበች ትገኛለች። እንዲሁም ለልጆች መጫወቻ እና መማሪያ የሚሆኑ የተለያዮ በእጇ የምታዘጋጃቸውን ነገሮች ለገበያ ታቀርባለች። ስለገጠሟት ተግዳሮቶች ፣ ከእናትነት ልምዷ ፣ እና ሌሎችም ነገሮችን አካፍላናለች።
መልካም ቆይታ!!
Instagram : aylas_playthingz
TikTok : Ayla's play thingz
Phone no. 0966922080
Store location: Gurd shola, Holy City Center building, Ground floor G-08
#enathood #እናትhood #የልጆች #ኢትዮጵያ #እናት #habesha #ethiopian #amharic #smallbusinessowner
| |||
| ከሆስፒታል ዉጪ ለመውለድ ከሩዋንዳ ወደ አሜሪካ ፤ ለምን? ከህይወቴ ታደሰ ጋር (MPH) | 08 May 2024 | 00:48:14 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ ታደሰ ጋር ስለ ሶስተኛ ልጇ የወሊድ ዝግጅት ፣ ለምን ከሩዋንዳ ወደ አሜሪካ ተጉዛ ከሚድዋይፍ ጋር ለመውለድ እንዳቀደች ፣ የእናትነት ጉዞዋን እና ለሎችም ተያያዥ ነገሮችን ተጨዋውተናል። በጣም ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች።
ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን።
ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት።
ህይወቴ የሶስት ልጆች እናት ናት። እንደ እቅድዋና ምኞትዋ ሶስተኛ ልጇን በ ማዋለጃ ማዕከል (Birthing Center) ፍፁም ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ ወልዳለች። እንኳን ደስ አለሽ እያልን በተከታታይ ስላካፈለችው ልምድ እናመሰግናታለን።
ህይወቴ በማህበረሰብ ጤና ማስተርስ አላት (Masters of Public Health) ጤናማ ተፈጥሮአዊ አኗኗር ላይ ትኩረት ታደርጋለች። ህይወቴ ጤናን ከተለመደው የህክምና እና በመድሀኒት ማከም በተለየ መልኩ አማራጭና ሁሉን አቀፍ የሆነ ወይም alternative and holistic health የተሟላ ጤና ፣ ከመርዛማ ንጥረ ነገሮች (toxins exposures) የነፃ አካባቢን በመፍጠር በሽታን እንዴት መቀነስና ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲያጎለብት የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በIG & YT ታካፍላለች።
በቤት በመሆን ሙሉ ጊዜዋን ሶስት ልጆችዋን እያሳደገች በሩዋንዳ ኪጋሊ ትኖራለች። በጊቢዋ የጓሮ አትክልቶች ትተክላለች ፣ ዶሮዎችን ታረባከች። እንዲሁም ከቤተሰቧ ጋር ጉዞ ማድረግ ታዘወትራለች። ልጆቿን ከአንድ በላይ ቋንቋ ለማስተማር የምትጥር ዘመነኛ ኑሮን ከባህል ጋር ያጣመረች እናት ናት።
| |||
| ወሊድ በአሜሪካ ከሆስፒታል ውጪ ፣ እናትነት ፣ ኑሮ በተለያየ አገር እና ጉዞ ከህይወቴ ታደሰ ጋር (ክፍል 1) | 01 May 2024 | 00:51:33 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ በቀለ ጋር ስለ ሶስተኛ እርግዝናዋ እንዴት ለወሊድ እየተዘጋጀች እንዳለች ፣ እናትነት ፣ በተለያዩ አገራትና ባህል ልጆችን ማሳደግ ፣ ወሊድ በሆስፒታል እና በማዋለጃ ማዕከል (birthing center) እና የመሳሰሉትን ነገሮች ተጨዋውተናል።
መልካም ቆይታ።
ህይወቴ የሶስት ልጆች እናት ናት። በማህበረሰብ ጤና ማስተርስ አላት (Masters of Public Health) ጤናማ ተፈጥሮአዊ አኗኗር ላይ ትኩረት ታደርጋለች። ህይወቴ ጤናን ከተለመደው የህክምና እና በመድሀኒት ማከም በተለየ መልኩ አማራጭና ሁሉን አቀፍ የሆነ ወይም alternative and holistic health የተሟላ ጤና ፣ ከመርዛማ ንጥረ ነገሮች (toxins exposures) የነፃ አካባቢን በመፍጠር በሽታን እንዴት መቀነስና ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲያጎለብት የሚረዱ ጠቃሚ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በIG & YT ታካፍላለች።
ህይወቴ በቤት በመሆን ሙሉ ጊዜዋን ልጆችዋን እያሳደገች በሩዋንዳ ኪጋሊ ትኖራለች። በጊቢዋ የጓሮ አትክልቶች ትተክላለች ፣ ዶሮዎችን ታረባከች። እንዲሁም ከቤተሰቧ ጋር ጉዞ ማድረግ ታዘወትራለች። ልጆቿን ከአንድ በላይ ቋንቋ ለማስተማር የምትጥር ዘመነኛ ኑሮን ከባህል ጋር ያጣመረች እናት ናት።
#ethiopian #habesha #amharic #ኢትዮጵያ #birth #childbirth #pregnancy
| |||
| ኦቲዝምና ተመሳሳይ ኑሮሎጂክ መዛባትን የሚረዳ አመጋገብ / A diet that helps with Autism and related disorder | 24 Apr 2024 | 01:10:29 | |
Our latest podcast opens the world of autism motherhood, where challenges meet triumphs, especially when raising a child with autism. Let’s discover together Sel Seyoum’s book on how a healing diet program tailored for autism can be a game-changer, offering crucial support and day to day management. From modern cities to remote corners of countries, families with children in the spectrum and related disorders find help and guidance in this dedicated book on nutrition, navigating the unique path of autism with strength and resilience.
Buy “Autism Lifestyle” handbook on Amazon 👉🏽 https://a.co/d/f3roRxl
👉🏽 Sel’s Instagram : [https://www.instagram.com/selseyoum](https://www.instagram.com/selseyoum?utm_source=ig_web_button_share_sheet&igsh=ZDNlZDc0MzIxNw==)
| |||
| የጥቁር እናት ነኝ ፀሀፊ እና ገጣሚ መሰረት ክንፈ ጋር የተደረገ ቆይታ - ስለ ኦቲዝም #autismawareness #enathood | 09 Apr 2024 | 01:29:07 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከመሰረት ክንፈ ጋር ስለ እናትነት ጉዞዋ ፥ ልዮ ፍላጎት ያለውን ልጅዋን ስታሳድግ የሚገጥማትን የለት ተለት ኑሮ ፥ ስለመፅሀፏ “የጥቁር እናት ነኝ” ፥ ስለምትሰራው የበጎ አድራጎት ስራ እና ሌሎችም ተጨዋውተናል።
መሰረት ክንፈ “የጥቁር እናት ነኝ” መፅሀፍ ፀሀፊ እና ገጣሚ ስትሆን የሁለት ወንድ ልጆች እናት ናት። የመጀመሪያ ልጇ ኦትስቲክ ወይም ልዮ ፍላጎት ያለሁ በመሆኑ የገጠማትን ውጣ ውረድ ፥ የህይወት እይታዋን እና ትዝታዎችዋን በግጥም አስውባ በማቅረብ ትታወቃለች። “የጥቁር እናት ነኝ” መፅሃፍ ሽያጭ ለበጎ አድራጎት በማዋል በኢትዮጵያ የሚገኙ የተቸረጉ እናቶችና ልጆችን እየረዳች ለብዙዎች መትረፍ ችላለች።
መልካም ቆይታ።
“የጥቁር እናት ነኝ” መፅሀፍ Amazon ላይ ይገኛል። 👉🏽 https://a.co/d/13Pp8Ys
#ethiopia #amharic #ethiopian #autism #እናት #ኢትዮጵያ #habesha
| |||
| ስለ ኦቲዝም ከሊያ ስዮም ከ Reaching Families ኘሬዝዳንት ጋር / Autism with Leah Seyum | 02 Apr 2024 | 01:21:35 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከሊያ ስዩም የ Reaching Families Advocacy and Support Group መስራችና ኘሬዝዳንት ጋር ስለ ኦቲዝም (ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆች) ሰፋ ያለ ውይይት አድርገናል።
ሊያ የግል የእናትነት ጉዞዋን እንዲሁም እየመራች ያለችው የበጎ አድራጎት ድርጅት ዉስጥ የሚሰሩ ስራዎች እና ማህበረሰባችን ስለ ኦቲዝም ማወቅ ያለበትን ሁሉ ከሙያ ልምዷ ጨምራ አካፍላናለች።
መልካም ቆይታ።
✨ሊያ ስዩም የአራት ልጆች እናት ስትሆን ሁለቱ ልጆችዋ ኦትስቲክ ወይም ልዩ ፍላጎት ያላቸው ናቸው።
በዚህም የተነሳ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆችን እና ወላጆችን የሚደግፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስርታ ዳላስ ቴክሳስን ጨምሮ በሌሎች ትላልቅ የአሜሪካ ግዛት ከተሞች ያሉ ኢትዮጵያን እና ኤርትራውያን ወገኖች በመደገፍ እና ድርጅቱን በኘሬዝዳንትነት በማገልገል ላይ ትገኛለች።
#autismawareness #enathood
Reaching Families Advocacy and Support Group
Website 👉🏾 https://reachfamilies.org/
Facebook 👉🏾 https://www.facebook.com/groups/454918007982318/
YouTube 👉🏾 https://youtube.com/channel/UCPOeeQv6d9qvXNJ2Gl0_94Q
| |||
| ስለ GAPS አመጋገብ እና በቤት ውስጥ ልጆችን ትምህርት ማስተማር ከሜላት ማሞ ጋር (MPH) ክፍል 2 - Gut & Psychology Syndrome | 17 Mar 2024 | 00:31:07 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ካለፈው የቀጠለ ዉይይት ከሜላት ማሞ ጋር ስለ GAPS አመጋገብና ልጆችን በቤት ውስጥ ስለማስተማር ተጨዋውተናል።
ሜላት በተከታታይ ሁለት ክፍሎች የልጇን የቆዳ ህመም (Eczema) ለማዳን እና ለቤተሰቧ ጤና የረዳትን የ GAPS (Gut and Psychology Syndrome) የአመጋገብ ልምድ ላይ ያላትን እውቀትና ልምድ እንዲሁም የለት ተለት ተሞክሮ አካፍላናለች።
ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት እርግጠኛ ነኝ። ሐሳብና አስተያየታችሁን ላኩልን። መልካም ቆይታ!!
ሜላት የሁለት ልጆች እናት ናት። በሙያዋ የማህበረሰብ ጤና ስፔሻሊስት እና licensed ASCP ናት።
በአሁን ጊዜ ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ በመሆን ልጆችዋን በማሳደግ እና ቤተሰብዋን በመንከባከብ ላይ ትገኛለች።
ማሳሰቢያ:- ይህ መረጃ የግል ልምድ እንደማስተማሪያ እንዲሆን የቀረበ ነው። የህክምና ምክር አይደለም። ለግል ጤና የህክምና ባለሙያ ያማክሩ!!
| |||
| ስለ GAPS አመጋገብ ፣ እናትነት እና ኑሮ በአቡዳቢ ከሜላት ማሞ (MPH, licensed ASCP) | 20 Feb 2024 | 01:08:24 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከሜላት ማሞ ጋር ስለ እናትነት ፣ በቤት ውስጥ ሙሉ ጊዜ መሆንና ቤተሰብን መንከባከብ ፣ እና ስለ ኑሮ በአቡዳቢ ተጨዋውተናል።
በሰፊው የልጇን የቆዳ ህመም (Eczema) ለማዳን እና ለቤተሰቧ ጤና የረዳትን የ GAPS (**Gut and Psychology Syndrome) የአመጋገብ ልምድ ላይ ያላትን እውቀትና ልምድ እንዲሁም የለት ተለት ተሞክሮ አካፍላናለች።** ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት እርግጠኛ ነኝ። መልካም ቆይታ!!
ሜላት የሁለት ልጆች እናት ናት። በሙያዋ የማህበረሰብ ጤና ስፔሻሊስት እና licensed ASCP ናት።
በአሁን ጊዜ ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ በመሆን ልጆችዋን በማሳደግ እና ቤተሰብዋን በመንከባከብ ላይ ትገኛለች።
ማሳሰቢያ:- ይህ መረጃ የግል ልምድ እንደማስተማሪያ እንዲሆን የቀረበ ነው። የህክምና ምክር አይደለም። ለግል ጤና የህክምና ባለሙያ ያማክሩ!!
| |||
| የቆዳ ውበት አጠባበቅ ፣ እራስን መንከባከብ እና እናትነት ከHanSim Skin ባለቤት ምልጃዬ ስሜ ጋር Skincare, Self-care, & Motherhood | 07 Dec 2023 | 01:01:05 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከምልጃዬ ስሜ የሃንሲም የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶች - HanSim Skin መስራች እና ባለቤት ጋር የፊትና የሰውነታችን ቆዳ እንዴት መንከባከብ እንደምንችል ተወያይተናል።
በተጨማሪም እራስን መጠበቅ እና እናትነት እንዴት አብሮ ማስኬድ ይቻላል የሚሉ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረናል።
የቢዝነስ ስራዎችዋን ከቤተሰብ ሃላፊነት ጋር እንዴት እንደምታስኬድ የግል ልምዷን ጨምራ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች።
መልካም ቆይታ።
የ HanSim ምርቶችን ለማግኘት:-
HanSim Online Store
👉🏾 https://hansimskin.com/
በአዲስ አበባ የሚገኙ መሸጫና አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ:-
1. የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶች መሸጫ :- ሌበኔዝ ህንፃ Lebenze Tower ጋዜቦ አደባባይ 1ኛ ፎቅ
2. Hansim Salon and Spa ሙሉ የፀጉር የውበት ሳሎን እና የቆዳ እንክብካቤ አገልግሎት :- ሆሊ ሲቲ ሴንተር Holy City Center 2ኛ ፎቅ ጉርድ ሾላ በስልክ ቁጥር 0931888855 ይደውሉ።
| |||
| ፍጹም ተፈጥሮአዊ ወሊድ በዉሃ ውስጥ ፤ የሶስተኛ ልጃችን የወሊድ ታሪክ - Super Natural Water Birth | 15 Nov 2023 | 00:12:20 | |
የዚህ ክፍል የእናትHood ፓድካስት ስለ ሶስተኛ ልጄ የወሊድ ታሪክ የተመለከተ ነው።
የወለድኩት በወሊድ ማእከል/birthing center ውስጥ ያለ ምንም መድሀኒት ፣ ፍፁም ተፈጥሮአዊ በሆነ መልኩ ከሚድዋይፎች እገዛ ጋር ነበር።
ለሁለተኛ ጊዜ ሰላም የሰፈነበት ወሊድ በዉሀ ዉስጥ ተሳክቶልኛል።
ቪዲዮን መመልከት ከፈለጋችሁ በYouTube ታገኙታላችሁ።
| |||
| የወሊድን ምጥ በኢፒዱራል አንስቴዚያ ወይስ ያለ ኢፒዱራል አንስቴዚያ Childbirth with Epidural Anesthesia vs without | 30 Sep 2023 | 00:16:49 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የወሊድ ምጥ በኢፒዱራል አንስቴዚያ (Epidural Anesthesia) ወይስ ያለ ኢፒዱራል አንስቴዚያ በሚል በሁለቱም መንገድ ያለኝ ልምድ አካፍያለሁ።
የመጀመሪያ ልጄን በኢፒዱራል አንስቴዚያ ስወልድ ያጋጠመኝን ፤ ሁለተኛ ልጄን ያለምንም መድሀኒት ስወልድ የነበረውን ሁኔታ በንፅፅር እና ሶስተኛ ለመውለድ እንዴት እየተዘጋጀሁ እንደሆነ ጨምሮ ተያያዝ ነገሮችን አንስቻለሁ። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ አደርጋለሁ።
መልካም ጊዜ!!
👉🏾 Everything You Need to Know about Epidural Anesthesia with Dr. Betelehem M. Asnake, MD – ስለ ኢፒዶራል አንስቴዚያ ዶ/ር ቤተልሔም አስናቀ
👉🏾 The Mama Natural Week-by-Week Guide to Pregnancy and Childbirth
👉🏾 Christian Hypo Birthing
| |||
| ስለ ኢፒዶራል አንስቴዚያ ከዶ/ር ቤተልሔም አስናቀ ጋር - Everything You Need to Know about Epidural Anesthesia | 15 Sep 2023 | 01:09:47 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል አንስቲዚኦሎጂስት ከሆነችው ዶ/ር ቤተልሔም አስናቀ ጋር ስለ ኢፒዶራል አንስቴዚያ/Epidural Anesthesia ማለትም በአብዛኛው ጊዜ በወሊድ እና በቀዶ ጥገና ጊዜ ስለሚሰጠው የማደንዘዣ መድሀኒት ተወያይተናል።
ሙያዊ ልምዷን ጨምራ በኢፒዶራል አንስቴዚያ ዙሪያ በተደጋጋሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች ሁሉ መልስና ማብራሪያ ሰጥታናለች። መልካም ቆይታ።
Dr. Betelehem M. Asnake, MD is a board certified Anesthesiologist and anesthesia global health director at the University of California Los Angeles.
👉🏾 Dr. Betelehem M. Asnake, MD - https://www.uclahealth.org/providers/betelehem-asnake
She is also a founder and manager of Mulu Mentor, which helps underrepresented and disadvantaged pre-medical students navigate the medical school application process through targeted mentorship.
👉🏾 Mulu Mentor - https://www.mulumentor.com/
| |||
| በእርግዝና ጊዜ ማጥባት እና ሁለት ልጆችን በጋራ ማጥባት - Breastfeeding during Pregnancy and Tandem Nursing | 02 Sep 2023 | 00:28:03 | |
በሶስት አመት የጡት ማጥባት ጉዞዬ ውስጥ ያደረግኩት በእርግዝና ጊዜ ማጥባት እና ሁለት ልጆችን በጋራ ማጥባት ብዙ ጥያቄና አስተያየት ያስተናገድኩበት ነው። ሳይንስ የሚለውን እና የራሴን ልምድ በዚህ ክፍል አካፍያለሁ። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ አደርጋለሁ።
💫 ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት።
🌟 የቀደሙ የጡት ማጥባት ዉይይቶች
👉🏾 የጡት ማጥባት ጥቅም ለልጆች https://youtu.be/WodjPq3RHJE?si=Pw9CGJajEzNrfeCs
👉🏾 የጡት ማጥባት ጥቅም ለእናቶች https://youtu.be/TVHwglULAD4?si=oKG_ePx44sxwLHQb
👉🏾 የእናት ጡት ወተት ማለብ ጠቃሚ ልምዶች https://youtu.be/YXb-DU9u2hM
| |||
| የእናት ጡት ወተት ማለብ ጠቃሚ ልምዶች ከብርቱካን አሊ (CRNA, DNP) - Breast Milk Pumping Best Practice | 27 Aug 2023 | 01:00:14 | |
የነሀሴን ወር የጡት ማጥባት ግንዛቤ ወር መሆኑን አስመልክተን በተከታታይ የጡት ማጥባት ዉይይቶችን እያደረግን በመሆኑ ከአድማጮች የተነሱ ስለ ጡት ወተት ማለብ እና አቆይቶ መጠቀም ጥያቄዎችን ከብርቱካን አሊ ጋር በመወያየት ከልምድና ከሙያዋ ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች።
ብርቱካን የሶስት ልጆች እናት ናት። በሙያዋ Certified Registered Nurse Anesthetist, (CRNA DNP) ማለትም ነርስ እና የማደንዘዣ ወይም የሰመመን መድሀኒት ሰጪ ናት።
🌟 በውይይታችን የተጠቀሱ ጡት ወተት ማለቢያ እና ማስቀመጫ
- Medela Breast Pump / የጡት ወተት ማለቢያ https://www.medela.us/breastfeeding/products/breast-pumps
- Spectra Breast Pump / የጡት ወተት ማለቢያ - [https://www.spectrababyusa.com](https://www.spectrababyusa.com/)
- Elvie Hand Free Portable Breast Pump / ተንቀሳቃሽ የጡት ወተት ማለቢያ - https://www.elvie.com/en-us/shop/elvie-pump
- WillowHand Free Portable Breast Pump / ተንቀሳቃሽ የጡት ወተት ማለቢያ - [https://onewillow.com](https://onewillow.com/)
- Mason Jar 4 oz / ጠርሙስ ለወተት ማስቀመጫ - https://amzn.to/47RdDZG
- Mason Jar 8 oz / ጠርሙስ ለወተት ማስቀመጫ - https://amzn.to/47RdDZG
- Pack It Ice Bag / የበረዶ ቦርሳ - https://amzn.to/3KXtJXE
- Breast Milk Warmer / የጡት ወተት ማሞቂያ - https://amzn.to/3Ebcfn0
| |||
| የእናት ጡት ወተት ጥቅም ለልጆች ከህይወቴ በቀለ (MPH) - Benefits of Breast Milk for Children | 13 Aug 2023 | 01:16:07 | |
የነሀሴን ወር የጡት ማጥባት ግንዛቤ ወር መሆኑን አስመልክተን በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ በቀለ ጋር ስለ የእናት ጡት ወተት ለልጆች ያለውን ጥቅም ተወያይተናል። እናም ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች።
በተጨማሪም በህይወቴ የYouTube channel ላይ ጡት ማጥባት ለእናቶች ያለውን ጥቅም። ተወያይተናል። በጣም ጥሩ መረጃዎችን የያዘ ነው። እንደተመለከቱት እጋብዛችሁአለሁ።
ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። እንዲሁም ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን።
💫ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ ወይም ለወዳጅ ለቤተሰብ አካፍሉት።
| |||
| የእናቶች ታሪክ በአለም ዙሪያ - ረቂቅ አዕምሮ ከዳላስ (Mother's Stories Around the World) | 28 Jul 2023 | 01:21:48 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ረቂቅ አዕምሮ የእናትነት ጉዞዋ አካፍላናለች። እናትነት ለሷ ምን ማለት እንደሆነ ፣ የዕለት ተለት ስኬትና ተግዳሮቶችን ጨምሮ እና ኑሮ በዳላስ ቴክሳስ ምን እንደሚመስል አጫውታናለች። መልካም ቆይታ።
ረቂቅ አዕምሮ የአንድ ቆንጆ ሴት ልጅ እናት ናት። ከባለቤቷ እና ከልጇ ጋር በቴክሳስ ዳላስ ትኖራለች። ሙሉ ጊዜዋን በቤት ውስጥ በመሆን ልጇን እና ቤተሰቧን ትንከባከባለች።
| |||
| የቤት ዉስጥ ት/ት፣ የሁለት ቋንቋ ተናጋሪነት እና ከስክሪን ነጻ የሆኑ ልጆች - Homeschooling, Bilingualism, and Screen free kids | 14 Jul 2023 | 01:03:46 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከቤተልሔም ፀጋዬ ጋር በቤት ውስጥ ልጆችን በሙሉ ሰዓት ማስተማር ፣ የሁለት ቋንቋ ተናጋሪ መሆን እና ልጆችን ከስክሪን (ከቲቪ እና ከስልክ) ነፃ አድርጎ ስለማሳደግ ተነጋግረናል። ቤተልሔም ብዙ ጠቃሚና አነቃቂ መረጃዎችን ከወላጅነት ልምዷ ጨምራ አካፍላናለች። መልካም ቆይታ።
ቤተልሔም የሁለት ልጆች እናት ስትሆን ልጆችዋን በሙሉ ጊዜ በቤትዋ ት/ቤት ሳትልክ ታስተምራለች። ልጆችዋ አማርኛ እና እንግሊዝኛ ቋንቋ አቀላጥፈው ይናገራሉ። ከዛም ጋር በተገናኘ የአማርኛ ቋንቋ ማስተማርያ የርቀት (በዙም) የምታስተምርበት ፋኖስ የሚባል ማስተማርያ አላት። በተጨማሪም ቤተልሔም የልጆች መማርያ መፅሀፍትንም ታዘጋጃለች። ከፋኖስ ድህረ ገፅ እነዚህን የአማርኛ መማርያ መፅሀፋትና ሌሎች መርጃ መሳሪያዎች ታገኛላችሁ። ሙሉ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ።
👉🏾 https://www.myfanos.com/
| |||
| የሚድዋይፈሪ (Midwifery) አገልግሎት በኢትዮጵያ ከረድኤት እንዳለው (Clinical midwife, Msc) -Midwifery care in Ethiopia | 23 Jun 2023 | 00:42:06 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከረድኤት እንዳለው ጋር ስለ ሚድዋይፈሪ (Midwifery) አገልግሎት ተወያይተናል። ለሴቶች እና እናቶች የሚሰጠውን አገልግሎት እንዲሁም በእርግዝና እና ወሊድ ጊዜ የሚድዋይፍ (Midwife) የሚሰጡትን እገዛ ጨምሮ ሌሎችም መረጃዎች አካፍላናለች። መልካም ቆይታ። ረድኤት እንዳለው በኢትዮጵያ የምትኖር ሚድዋይፍ (Clinical midwife, Msc) ናት። በአቻሞ ዩንቨርስቲ አስተማሪ ናት። እማ ዛሬ (Ema Zaire) በሚባል የYoutube channel ስለእናቶች እና የልጆች ጤና ጠቃሚ መረጃዎችን ታካፍላለች። እዚህ ጋር ልታገኙት ትችላላችሁ 👉🏾 https://youtube.com/@emazare6315
| |||
| ጤናማ ኑሮ እና ከመርዛማ ንጥረ ነገር የፀዳ የአኗኗር ዘይቤ ከህይወቴ በቀለ (MPH) - Healthy & non toxic living | 13 Jun 2023 | 01:16:14 | |
በዚህ የእናትHood ፓድካስት ክፍል የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ (MPH) ከሆነችው ከህይወቴ በቀለ ጋር ስለ ጤናማ ኑሮ እና ከመርዛማ ንጥረ ነገር የፀዳ የአኗኗር ዘይቤ ተወያይተናል። በጣም ብዙ ጠቃሚ መረጃዎችን አካፍላናለች።
ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን። ጥያቄ ካላችሁም ብትልኩልን እንመልሳለን።
ተመልክታችሁ ወይም አድምጣችሁ ከወደዳችሁት ለጓደኛ፣ ለወዳጅ ወይም ለቤተሰብ አካፍሉት።
| |||
| የእናቶች የአዕምሮ ጤና ከሊዲያ ዱሜሳ (Ph.D.) ጋር የተደረገ ዉይይት - Maternal Mental Health | 01 Jun 2023 | 00:44:00 | |
ከክሊኒካል ሳይኮሎጆስት ሊዲያ ዱሜሳ (Ph.D.) ጋር ስለ እናቶች የአዕምሮ ጤና ተወያይተናል። ከእርግዝና እስከ አንድ አመት ድህረ ወሊድ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የአዕምሮ ጤና ችግሮች እና ምልክቶቻቸው ፣ እርዳታ እንዴት ማግኘት እንደምንችል እናም የማህበረሰብ ድጋፍ ጥቅምን ጨምሮ ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮች ተነጋግረናል። መልካም ቆይታ።
👉🏾 ከሊዲያ ዱሜሳ (Ph.D.) አገልግሎት (therapy) ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ በመጠቀም ስልክ ፣ ኢሜል እና አድራሻ ያግኙ።
https://www.psychologytoday.com/us/therapists/lediya-dumessa-washington-dc/796462
| |||
| ልጆች ተኮር አመጋገብ (Baby - Led Weaning) ከጊፍቲ ባዮ ጋር የተደረገ ቆይታ | 23 May 2023 | 01:06:14 | |
በዛሬው የእናትHood ፓድካስት ክፍል ከጊፍቲ ባዮ ጋር ቆይታ ይኖረናል። ዉይይታችን የህፃናት ልጆች አመጋገብ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። ህፃናት ልጆች በተለይም ከስድስት ወር በኃላ ተጨማሪ ምግብ እንዴት እናስጀምራለን? ምን አይነት የአመጋገብ ዘዴዎች አሉ? ፣ እንዲሁም እንዴት ተመጣጣኝ ምግብ መመገብ እንችላለን? እና ህፃናት እራሳቸውን መመገብ እንዲችሉ እንዴት መርዳት እንምንችል ጨምሮ ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮችን እናነሳለን።
| |||
| እናትHood ፖድካስት - እንኳን ደህና መጣችሁ!! Welcome to EnatHood!! | 05 May 2023 | 00:03:14 | |
እናትHood ፖድካስት ስለ እናትነትና እና እናት ስለሚመለከታት ሁሉ ነገር ላይ ትኩረት የሰጠ ፖድካስት ነው።
እርግዝና ፣ ወሊድ ፣ የልጅ እንክብካቤ ፣ ወላጅነት እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ምርጫዎችን ጨምሮ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ይሸፍናል።
ተዘጋጅቶ የሚቀርበው በሐና ኃይሌ ከ enathood.com ጦማር ነው።
EnatHood is a podcast dedicated to motherhood and what a mother cares for.
It covers a range of topics, including pregnancy, childbirth, baby care, parenting, and healthy lifestyle choices.
It is brought to you by Hana Haile from enathood.com.
| |||